ኢዮብ 28:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብረትም ከመሬት ውስጥ ይወጣል፤ መዳብም እንደ ድንጋይ ይፈለጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብረት ከመሬት ውስጥ ይገኛል፤ መዳብም ከማዕድን ድንጋይ ቀልጦ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፥ ከቀለጠ ድንጋይም መዳብ ይወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብረት ከመሬት ይገኛል፤ መዳብም ከማዕድን ድንጋይ ቀልጦ ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ብረት ከመሬት ውስጥ ይወሰዳል፥ መዳብም ከድንጋይ ይቀለጣል። |
አሁንም፥ እነሆ፥ በድህነቴ ለእግዚአብሔር ቤት መቶ ሺህ መክሊት ወርቅና አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፥ ሚዛንም የሌላቸው ብዙ ናስና ብረት አዘጋጅቻለሁ፤ ደግሞም የማይቈጠር ብዙ የዝግባ እንጨትና ድንጋዮች አዘጋጅቻለሁ፤ አንተም ልጄ ከዚያ በላይ ጨምር።
ሳይጐድልህ እንጀራን ወደምትበላባት፥ አንዳችም ወደማታጣባት ምድር፥ ድንጋይዋ ብረት ወደ ሆነ፥ ከተራራዋም መዳብ ወደሚማስባት ምድር ያገባሃል።