ኢዮብ 27:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤቱ እንደ ሸረሪት ድር፥ ቅንቅንም እንደሚበላው ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር፣ እህል ጠባቂም እንደ ቀለሰው መጠለያ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር፥ ጠባቂም እንደሚሠራው ጎጆ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድርና እንደ ሰብል ጠባቂ ጎጆ ይፈራርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር ይሠራል፥ ጠባቂም እንደሚሠራው ጎጆ ነው። |
የቀረውንም ኑሬዬን አጣሁ። ከእኔም ወጣች፥ ተለየችም። ድንኳኑን ተክሎ እንደሚያድርና እንደሚሄድ፥ ሊቈረጥ እንደ ተቃረበ ሸማም እንዲሁ ነፍሴ በላዬ ሆነች።
እንደ ልብስ ፈጥነው ያረጃሉና አይቈዩም፤ ብል እንደ በላውም ይሆናሉ፤ ጽድቄ ግን ለዘለዓለም፥ ማዳኔም ለልጅ ልጅ ይሆናል።
ዋው። ማደሪያውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓሉን ሁሉ አጠፋ፤ እግዚአብሔር በጽዮን ያደረገውን በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፤ በቍጣውም መዓት ነገሥታቱን፥ አለቆቹንና ካህናቱን አጠፋ።