ኢዮብ 27:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእርሱ ዘንድስ ባለሟልነትን ያገኛልን? እግዚአብሔርንስ በጠራ ጊዜ ይመልስለታልን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁሉን ቻይ አምላክ ደስ ይለዋልን? ዘወትርስ እግዚአብሔርን ይጠራልን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁሉን በሚችል አምላክ ይደሰታሉን? በየጊዜውስ የእግዚአብሔርን ስም ይጠራሉን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን? |
በዚያን ጊዜ በእግዚአብሔር ትታመናለህ፤ በምድርም በረከት ላይ ያወጣሃል፤ የአባትህ የያዕቆብንም ርስት ይመግብሃል፤ የእግዚአብሔር አፍ እንደዚህ ተናግሮአልና።
እርሱም ጻድቅና ከነቤተ ሰቡ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነበር፤ ለሕዝቡም ብዙ ምጽዋት ይሰጥ ነበር፤ ዘወትርም ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር።