ኢዮብ 26:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፥ በማስተዋሉም ዐንበሪውን ይገለብጠዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኀይሉ ባሕርን ያናውጣል፤ በጥበቡም ረዓብን ይቈራርጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኃይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፥ በማስተዋሉም ረዓብን ይመታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኀይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፤ በጥበቡም ረዓብ የተባለውን ታላቅ አውሬ ያጠፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኃይሉ ባሕርን ጸጥ ያደርጋል፥ በማስተዋሉም ረዓብን ይመታል። |
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፤ እነርሱም ይዋረዳሉ፤
ባሕርን የማናውጥ፥ ሞገዱም እንዲተምም የማደርግ አማላክሽ እግዚአብሔር እኔ ነኝና፥ ስሜም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።
ስሙ የሠራዊት ጌታ የሚባል፥ ፀሐይን በቀን፥ ጨረቃንና ከዋክብትንም በሌሊት ብርሃን አድርጎ የሚሰጥ፥ እንዲተምሙም የባሕርን ሞገዶች የሚያናውጥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦