Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 31:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የሚ​ባል፥ ፀሐ​ይን በቀን፥ ጨረ​ቃ​ንና ከዋ​ክ​ብ​ት​ንም በሌ​ሊት ብር​ሃን አድ​ርጎ የሚ​ሰጥ፥ እን​ዲ​ተ​ም​ሙም የባ​ሕ​ርን ሞገ​ዶች የሚ​ያ​ና​ውጥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 በቀን እንድታበራ፣ ፀሓይን የመደበ፣ በሌሊት እንዲያበሩ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ያዘዛቸው፣ የሞገዱ ድምፅ እንዲተምም፣ ባሕሩን የሚያናውጥ፣ ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ እንዲህ ይላል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ስሙ የሠራዊት ጌታ የሚባል፥ ፀሐይን በቀን የጨረቃንና የከዋክብትን የማይዛነፍ ሥርዓት በሌሊት ብርሃን አድርጎ የሚሰጥ፥ እንዲተምሙም የባሕርን ሞገዶች የሚያናውጥ ጌታ እንዲህ ይላል፦

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ፀሐይን በቀን እንዲያበራ የሚያደርገው፥ ጨረቃና ከዋክብት በሌሊት እንዲያበሩ ሥርዓትን የወሰነላቸው፥ ባሕሩን በማዕበል እንዲናወጥ የሚቀሰቅሰው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ስሙም የሠራዊት አምላክ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ስሙ የሠራዊት ጌታ የሚባል፥ ፀሐይን በቀን የጨረቃንና የከዋክብትን ሥርዓት በሌሊት ብርሃን አድርጎ የሚሰጥ፥ እንዲተምሙም የባሕርን ሞገዶች የሚያናውጥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 31:35
39 Referencias Cruzadas  

የያ​ዕ​ቆብ ዕድል ፈንታ እንደ እነ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ ሁሉን የፈ​ጠረ ነውና እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ነገድ ነውና፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


ባሕ​ርን የማ​ና​ውጥ፥ ሞገ​ዱም እን​ዲ​ተ​ምም የማ​ደ​ርግ አማ​ላ​ክሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝና፥ ስሜም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


የሚ​ቤ​ዢ​አ​ቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ምድ​ርን ያሳ​ርፍ ዘንድ፥ በባ​ቢ​ሎ​ንም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ያውክ ዘንድ ጠላ​ቶ​ቹን ወቀሳ ይወ​ቅ​ሳ​ቸ​ዋል።


ፈጣ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ታዳ​ጊሽ ነው፤ እር​ሱም በም​ድር ሁሉ እን​ደ​ዚሁ ይጠ​ራል።


ወደ ሰማይ አት​መ​ል​ከት፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሁሉ በታች ላሉት አሕ​ዛብ ሁሉ የሰ​ጣ​ቸ​ውን ፀሐ​ይ​ንና ጨረ​ቃን፥ ከዋ​ክ​ብ​ት​ንና የሰ​ማ​ይን ሠራ​ዊት ሁሉ አይ​ተህ፥ ሰግ​ደ​ህ​ላ​ቸው፥ አም​ል​ከ​ሃ​ቸ​ውም እን​ዳ​ት​ስት ተጠ​ን​ቀቅ።


የያ​ዕ​ቆብ ዕድል ፋንታ እንደ እነ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ እርሱ የሁሉ ፈጣሪ ነውና። እስ​ራ​ኤ​ልም የር​ስቱ ነገድ ነው። ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


እኔ ሕያው ነኝና በተ​ራ​ሮች መካ​ከል እን​ዳለ እንደ አጤ​ቤ​ር​ዮን፥ በባ​ሕ​ርም አጠ​ገብ እን​ዳለ እንደ ቀር​ሜ​ሎስ፥ እን​ዲሁ በእ​ው​ነት ይመ​ጣል፥ ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የሆነ ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ታላ​ቅና ኀያል አም​ላክ ሆይ! ለብዙ ሺህ ምሕ​ረ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ የአ​ባ​ቶ​ች​ንም በደል ከእ​ነ​ርሱ በኋላ በል​ጆ​ቻ​ቸው ብብት ትመ​ል​ሳ​ለህ።


በውኑ እኔን አት​ፈ​ሩ​ምን? ከፊ​ቴስ አት​ደ​ነ​ግ​ጡ​ምን? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እን​ዳ​ያ​ልፍ አሸ​ዋን በዘ​ለ​ዓ​ለም ትእ​ዛዝ ለባ​ሕር ዳርቻ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ ሞገ​ዱም ቢት​ረ​ፈ​ረ​ፍና ቢጮኽ ከእ​ርሱ አያ​ል​ፍም።


በሙ​ሴም ቀኝ እጅ ውኃ​ውን ከፈ​ልሁ፤” ውኃ​ውም ተከ​ፍሎ በፊቱ ጸና፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም አደ​ረ​ገ​ለት።


በቅ​ድ​ስት ከተማ ስም የተ​ጠ​ራ​ችሁ፥ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ባል በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የም​ት​ደ​ገፉ፥ ይህን ስሙ።


የተ​ራ​በ​ችን ነፍስ አጥ​ግ​ቦ​አ​ልና፥ የተ​ራ​ቈ​ተ​ች​ንም ነፍስ በበ​ረ​ከት ሞል​ቶ​አ​ልና።


ተራ​ሮች ሳይ​ወ​ለዱ፥ ምድ​ርም ዓለ​ምም ሳይ​ሠሩ፥ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም ድረስ መቼም መች አንተ ነህ።


እኛ ሕዝ​ብህ ግን፥ የማ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ህም በጎች፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እና​መ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለን፤ ለልጅ ልጅም ምስ​ጋ​ና​ህን እን​ና​ገ​ራ​ለን።


ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ውን አውቅ ዘንድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ እስ​ክ​ገባ ድረስ፥


በድ​ካ​ምም ጠላት አል​ሆ​ኑም። ከሰው ጋርም አል​ተ​ገ​ረ​ፉም።


በኀ​ይሉ ባሕ​ርን ጸጥ ያደ​ር​ጋል፥ በማ​ስ​ተ​ዋ​ሉም ዐን​በ​ሪ​ውን ይገ​ለ​ብ​ጠ​ዋል።


የሰ​ማ​ይን ሥር​ዐት፥ ከሰ​ማይ በታ​ችስ የሚ​ሆ​ነ​ውን ታው​ቃ​ለ​ህን?


ለዘ​ለ​ዓ​ለም አቆ​ማ​ቸው፤ ትእ​ዛ​ዝን ሰጣ​ቸው፥ አላ​ለ​ፉ​ምም።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ቀንና ሌሊት በወ​ራ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ሆኑ የቀን ቃል ኪዳ​ኔ​ንና የሌ​ሊት ቃል ኪዳ​ኔን ማፍ​ረስ ብት​ችሉ፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የቀ​ንና የሌ​ሊት ቃል ኪዳ​ኔን የሰ​ማ​ይ​ንና የም​ድ​ር​ንም ሥር​ዐት ያላ​ጸ​ናሁ እንደ ሆነ፥


ከሲ​ኦል እጅ እታ​ደ​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከሞ​ትም እቤ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ሞት ሆይ! መው​ጊ​ያህ ወዴት አለ? ሲኦል ሆይ! ድል መን​ሣ​ትህ ወዴት አለ? ደስ​ታህ ከዐ​ይ​ኖ​ችህ ተሰ​ወ​ረች።


እነሆ የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች በኀ​ጢ​አ​ተኛ መን​ግ​ሥት ላይ ናቸው፤ ከም​ድ​ርም ፊት አጠ​ፋ​ታ​ለሁ፤ ነገር ግን የያ​ዕ​ቆ​ብን ቤት ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እኔም ደግሞ በአ​ብ​ር​ሃ​ምና በይ​ስ​ሐቅ በያ​ዕ​ቆ​ብም ዘር ላይ ገዢ​ዎች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እን​ዳ​ላ​ስ​ነሣ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንና የባ​ሪ​ያ​ዬን የዳ​ዊ​ትን ዘር እጥ​ላ​ለሁ፤ ምር​ኮ​አ​ቸ​ውን እመ​ል​ሳ​ለ​ሁና፥ እም​ራ​ቸ​ው​ማ​ለ​ሁና።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios