ኢዮብ 24:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ በውኃ ፊት ላይ በርሮ ያልፋል፤ እድል ፋንታውም በምድር ላይ የተረገመች ናት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይሁን እንጂ፣ በውሃ ላይ የሚኵረፈረፍ ዐረፋ ናቸው፤ የወይን ቦታው ሰው የማይደርስበት፣ ርስታቸው ርጉም ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እነርሱ በውኃ ላይ ተንሳፈው ያልፋሉ፥ ድርሻቸውም በምድር ላይ የተረገመች ናት፥ ወደ ወይኑ ቦታ መንገድ አይመለሱም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሆኖም እነርሱ በውሃ ላይ እንደሚታይ ዐረፋ ለጥቂት ጊዜ ብቻ ይታያሉ፤ ርስታቸው የተረገመ ይሆናል፤ ወደ ወይን ተክል ቦታቸውም ማንም አይሄድም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ በውኃ ፊት ላይ በርረው ያልፋሉ፥ እድል ፈንታቸውም በምድር ላይ የተረገመች ናት፥ ወደ ወይኑ ቦታ መንገድ አይዞሩም። |
“የራሳቸው ያልሆነውን እርሻ ያለ ሰዓቱ ያጭዳሉ። ኃጥኣን ድሆችን በወይናቸው ቦታ ያለ ዋጋና ያለ ቀለብ ያሠሩአቸዋል።
የመርከብ መንገድ ፍለጋ፥ ወይም የሚበርና የሚበላውን የሚፈልግ የንስር ፍለጋ እንደማይታወቅ ሕይወቴ እንዲሁ ሆነ።
ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድዳባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፣ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።