ኢዮብ 23:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነትና ቅንነት ከእርሱ ዘንድ ናቸውና። ከፍርዴም ለዘለዓለም ያሳርፈኝ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቅን ሰው ጕዳዩን በርሱ ፊት ያቀርባል፤ እኔም ከፈራጄ ለዘላለም ነጻ እሆናለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚከራከረው ቅን ሰው መሆኑን ይመሰክር ነበር፥ እኔም በፈራጅ ፊት ለዘለዓለም ነፃ እወጣ ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያ ቅን ሰው ከእርሱ ጋር ይከራከራል፤ ዳኛዬ እግዚአብሔርም ለዘለዓለም ነጻ ያወጣኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቅን ሰው ከእርሱ ጋር በዚያ ይከራከር ነበር፥ እኔም ከፈራጄ ለዘላለም እድን ነበር። |
“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ።
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኀጢአተኞች መንገድ ስለ ምን ይቀናል? በደልንስ የሚያደርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላቸዋል?
ቍጣው ለዘለዓለም ይኖራልን? እስከ ፍጻሜስ ድረስ ይጠብቀዋልን? እነሆ እንዲህ ብለሽ ተናገርሽ፤ እንደ ተቻለሽም መጠን ክፉን ነገር አደረግሽ።”