ኢዮብ 22:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብርሃኑም ጨለማ ሆነብህ፥ ተኝተህም ሳለህ ውኃው አሰጠመህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዳታይ ጨለማ የሆነብህ፣ ጐርፍም ያጥለቀለቀህ ለዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዳታይ ብርሃን ጨለማ ሆነችብህ፥ የውኆችም ሙላት አሰጠመህ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማየት እስከሚሳንህ ድረስ ጨለማ ወርሶሃል፤ የጐርፍ ውሃም አጥለቅልቆሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዳታይ ብርሃን ጨለማ ሆነችብህ፥ የውኆችም ብዛት አሰጠመህ። |
ወደ ታችም ወደ ምድር ትመለከታላችሁ፤ ድቅድቅ ጨለማንም ታያላችሁ፤ ታላቅ መከራንም ትቀበላላችሁ፤ ትጨነቃላችሁ፤ ትቸገራላችሁም፤ በፊታችሁም ጨለማ ይሆናል፤ አታዩምም፤ በመከራም ያለ ጊዜው እስኪደርስ አይድንም።
“በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ በሲኦልም ሆድ ውስጥ የጩኸቴን ድምፅ ሰማኝ፤ ቃሌንም አዳመጥህ።