ኢዮብ 21:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዘራቸው በፊታቸው ከእነርሱ ጋር ጸንቶ ይኖራል፤ ልጆቻቸውም በዐይናቸው ፊት ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዘራቸው በዐይናቸው ፊት፣ ልጆቻቸውም በዙሪያቸው ጸንተው ሲኖሩ ያያሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ጸንቶ ይኖራል፥ ልጆቻቸውም በዓይናቸው ፊት ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው አድገውና ተደላድለው ሲኖሩ ለምን ያያሉ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ጸንቶ ይኖራል፥ ልጆቻቸውም በዓይናቸው ፊት ናቸው። |
ቤታቸው በብልፅግና የተሞላ ነው፤ የሚያስፈራቸውም የለም። ከእግዚአብሔርም ዘንድ መቅሠፍት አይመጣባቸውም።