ቢጠብቃትም፥ ባይተዋትም፤ በጕሮሮውም መካከል ቢይዛት፥ መብሉ በአንጀቱ ውስጥ ይገላበጣል፤
አውጥቶ ለመጣል እየሳሳ፣ በአፉ ውስጥ ቢያቈየው፣
ቢጠብቀውም ባይተወውም፥ በጉሮሮውም ቢይዘው፥
እንዳያልቅበትም በአፉ ይዞ እያላመጠ ቢያቈየውም፥
ቢጠብቀውም ባይተወውም፥ በጕሮሮውም ቢይዘው፥
ፈጽሞ ራሱን መርዳት አይችልም። የእፉኝትም መርዝ ከከንፈሩ በታች አለ።
“ሆዱን ቢያጠግብ፥ የመዓት መቅሠፍት ይጨመርበታል፤ የሕማሙም ሥቃይ ይጸናበታል።
ለአላዋቂ ልጅ የሚዋስ ፍርድን ያስነቅፋል፥ የኃጥኣንም አፍ ክፉ ቅጣትን ይውጣል።
ሥጋውም ገና በጥርሳቸው መካከል ሳለ ሳያኝኩትም፥ እግዚአብሔር ሕዝቡን እጅግ ታላቅ በሆነ መቅሠፍት አጠፋቸው።
እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞታላችሁ፤ ነገር ግን በመንፈሳዊ ሥራ የሥጋችሁን ፈቃድ ብትገድሉ ለዘለዓለም በሕይወት ትኖራላችሁ።