ኢዮብ 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጭንቀት በአጥንቶቹ ሞልቶአል፤ ነገር ግን ሕማሙ ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐጥንቱን የሞላው የወጣትነት ብርታት፣ ከርሱ ጋራ በዐፈር ውስጥ ይተኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አጥንቶቹ በወጣት ኃይል ተሞልተው ነበር፥ ነገር ግን አሁን ያ የወጣትነት ኃይሉ ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይል የተሞላው የወጣትነት ሰውነቱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ዐፈር ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አጥንቶቹ ብላቴንነቱን ሞልተዋል፥ ነገር ግን ከእርሱ ጋር በመሬት ውስጥ ይተኛል። |
በርኵሰትሽ ሴሰኝነት አለ፤ አነጻሁሽ፤ አልነጻሽምና መዓቴን በላይሽ እስክጨርስ ድረስ እንግዲህ ከርኵሰትሽ አትነጺም።
በሕያዋንም ምድር ኀያላኑን ያስፈሩ ነበርና፤ መሣሪያቸውን ይዘው ወደ ሲኦል ከወረዱ፥ ሰይፋቸውንም ከራሳቸው በታች ከአደረጉ፥ ኀጢአታቸውም በአጥንታቸው ላይ ከሆነ ጋር ከወደቁ ካልተገረዙ ኀያላን ጋር ይተኛሉ።
ዳግመኛም ጌታችን ኢየሱስ፥ “እኔ እሄዳለሁ ትሹኛላችሁም፤ ነገር ግን አታገኙኝም፤ በኀጢኣታችሁም ትሞታላችሁ፤ እኔ ወደምሄድበትም እናንተ መምጣት አይቻላችሁም” አላቸው።