እነርሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
ኢዮብ 19:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወዮልኝ! አፋችሁን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ታደርጋላችሁና፤ ትጓደዱብኛላችሁ፤ ትዘልፉኛላችሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ራሳችሁን በእኔ ላይ ከፍ ብታደርጉ፣ መዋረዴንም እኔን ለመሞገት ብትጠቀሙበት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእውነትም ብትኩራሩብኝ፥ በመዋረዴም ብታሳብቡ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት እናንተ ራሳችሁን ከፍ ከፍ አድርጋችሁ፥ የእኔን መዋረድ የመከራከሪያ ነጥብ ታደርጉታላችሁ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእውነትም ብትጓደዱብኝ፥ መዋረዴን በእኔ ላይ ብትከራከሩ፥ |
እነርሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከምርኮ የተረፉት ቅሬታዎች በታላቅ መከራና ስድብ አሉ፤ የኢየሩሳሌምም ቅጥር ፈርሶአል፥ በሮችዋም በእሳት ተቃጥለዋል” አሉኝ።
በእውነት እኔ ከበደልሁ፤ ስሕተቴ ከእኔ ጋር ትኖራለች። የማላውቀውንም ነገር ተናገርሁ፤ ነገሬም ስንፍና ነው እንጂ በየጊዜው አይደለም።
ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኀኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
ነፍሴን ከሞት፥ ዐይኖቼን ከዕንባ፥ እግሮቼንም ከድጥ አድነሃልና፥ በሕያዋን ሀገር እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው ዘንድ።
በዚያም ቀን ሰባት ሴቶች፥ “የገዛ እንጀራችንን እንበላለን፤ የገዛ ልብሳችንንም እንለብሳለን፤ ስምህ ብቻ በእኛ ላይ ይጠራ፤ መሰደባችንንም አርቅልን” ብለው አንዱን ወንድ ይይዙታል።
ደቀ መዛሙርቱም፥ “መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕዉር ሆኖ የተወለደው በማን ኀጢኣት ነው? በራሱ ነውን? ወይስ በወላጆቹ?” ብለው ጠየቁት።
እንደ መከራዋና እንደ ኀዘንዋም እግዚአብሔር ልጅ አልሰጣትም ነበር። ስለዚህም ታዝን ነበር። እግዚአብሔር ማኅፀንዋን ዘግትዋልና፥ ልጆችንም አልሰጣትምና።