ኢዮብ 18:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የኀጢኣተኞች መብራት ይጠፋል፥ ነበልባላቸውም ብልጭ አይልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የክፉዎች መብራት ይጠፋል፤ የእሳቱም ነበልባል ድርግም ይላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥ የእሳቱም ነበልባል ብልጭ አይልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፤ የእሳቱም ነበልባል ዳግመኛ አይታይም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኃጢአተኛ መብራት ይጠፋል፥ የእሳቱም ነበልባል ብልጭ አይልም። |
መከራው ይገባሃል፤ አንተስ የሞትህ እንደ ሆነ ምንድን ነው? ከሰማይ በታች ምድር ስለ አንተ ባድማ ትሆናለችን? ወይስ ተራራዎች ከመሠረታቸው ይናወጣሉን?
ለጻድቃን ሁልጊዜ ብርሃን ነው፤ የኃጥኣን መብራት ግን ትጠፋለች። የሐሰተኞች ነፍሳት በኀጢአት ይስታሉ። ጻድቃን ግን ይራራሉ፥ ይመጸውታሉም።
እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ፥ የእሳትንም ነበልባል ከፍ ያደረጋችሁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ብርሃንና ባነደዳችሁት ነበልባል ሂዱ፤ ስለ እኔ ይህ ይሆንባችኋል፤ በኀዘንም ትተኛላችሁ።
በጠፋህም ጊዜ ሰማዮችን እሸፍናለሁ፤ ከዋክብትንም አጨልማለሁ፤ ፀሐዩንም በደመና እሸፍናለሁ፤ ጨረቃም ብርሃኑን አይሰጥም።