ኢዮብ 16:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን በእጄ ዐመፅ የለም፤ ጸሎቴም ንጹሕ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምድር ሆይ፤ ደሜን አትሸፍኚ፤ ጩኸቴም ማረፊያ አያግኝ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ምድር ሆይ፥ ደሜን አትክደኚ፥ ለጩኸቴም ማረፊያ አይኑር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ምድር ሆይ! የደረሰብኝን በደል አትሸፍኚ! ስለ ፍትሕ የማቀርበው አቤቱታ ተሸፍኖ እንዲቀር አታድርጊ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድር ሆይ፥ ደሜን አትክደኚ፥ ለጩኸቴም ማረፊያ አይሁን። |
እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና።
እነሆ፥ እግዚአብሔር በምድር በሚኖሩት ላይ ከመቅደሱ መቅሠፍቱን ያመጣል፤ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፤ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።
ደምዋም በመካከልዋ አለ። በተራቈተ ድንጋይ ላይ አደረገችው እንጂ በአፈር ይከደን ዘንድ በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም።