ኢዮብ 16:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቍርበቴ ላይ ማቅ ሰፉ፤ መከራዬ በመሬት ላይ በዛች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀልቷል፤ ጨለማም በዐይኖቼ ቆብ ላይ ዐርፏል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፥ የሞት ጥላ በዐይኖቼ ቆብ ላይ አለ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፊቴ በልቅሶ ቀላ ድቅድቅ ጨለማም ቅንድቦቼን ሸፈናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፊቴ ከልቅሶ የተነሣ ቀላ፥ የሞት ጥላ በዓይኖቼ ቆብ ላይ አለ፥ |
ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጕሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።
ዔ። የሚያጽናናኝ፥ ነፍሴንም የሚመልሳት ከእኔ ርቆአልና ዐይኔ ውኃ ያፈስሳል። ጠላት በርትቶአልና ልጆች ጠፍተዋል።