“የማይበድልም ሰው የለምና አንተን ቢበድሉ፥ ተቈጥተህም ለጠላቶቻቸው አሳልፈህ ብትሰጣቸው፥ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ወደ ጠላቶች ሀገር ቢማረኩም፥
ኢዮብ 15:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሟች ሰው ማን ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ፣ ከሴት የተወለደ ምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከንጹሕ ለመመደብ የሰው ልጅ ምንድነው? ጻድቅስ ለመባል ከሴት የተወለደ ምንድነው? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ሰው ንጹሕ ሊሆን ይችላልን? ሥጋ ለባሽስ ጻድቅ ሊሆን ይችላልን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ጻድቅስ ይሆን ዘንድ ከሴት የተወለደ ምንድር ነው? |
“የማይበድልም ሰው የለምና አንተን ቢበድሉ፥ ተቈጥተህም ለጠላቶቻቸው አሳልፈህ ብትሰጣቸው፥ ሩቅ ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ወደ ጠላቶች ሀገር ቢማረኩም፥
“የማይበድል ሰው የለምና አንተን ቢበድሉ፥ ብትቈጣቸውም፥ ለጠላቶቻቸውም አሳልፈህ ብትሰጣቸው፥ ሩቅም ወይም ቅርብ ወደ ሆነ ሀገር ጠላቶቻቸው ቢማርኩአቸው፥
የሚምረኝ፥ መሸሸጊያዬ፥ መጠጊያዬና አዳኜ፤ መታመኛዬም፤ እርሱን ታመንሁ፤ ሕዝቡንም ከእኔ በታች የሚያስገዛልኝ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለዘለዓለም ያፈርስሃል፤ ከቤትህም ይነቅልሃል፥ ያፈልስሃልም፥ ሥርህንም ከሕያዋን ምድር።
እግዚአብሔር በጊዜው ሰዎችን ቅኖች አድርጎ እንደ ሠራቸው እነሆ፥ ይህን ብቻ አገኘሁ፥ እነርሱ ግን ብዙ ዕውቀትን ይሻሉ።
በእኔ ማለት በሥጋዬ መልካም ነገር እንደማይኖር አውቃለሁ፤ መልካም ሥራ ለመሥራት መሻቱስ በእኔ ዘንድ አለ፤ በጎ ምግባር መሥራት ግን የለኝም።
ነገር ግን ተስፋ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ይሆን ዘንድ፥ ያመኑትም ያገኙት ዘንድ፥ መጽሐፍ ሁሉን በኀጢአት ዘግቶታል።