ኢዮብ 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እንደ ምንደኛ ሕይወቱን እንዲጠባበቃት፥ ያርፍ ዘንድ ከእርሱ ዘወር በል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ ዘመኑን እንደ ምንደኛ እስኪፈጽም ድረስ፣ ፊትህን ከርሱ መልስ፤ ተወው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ምንደኛ ዕድሜው እስኪፈጸም ድረስ ያርፍ ዘንድ ከእርሱ ጥቂት ዘወር በል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቅጥረኛ የቀን ሥራውን ሲፈጽም እንደሚደሰት፥ ሰውም በድካም ዘመኑ እንዲደሰት ታገሠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ምንደኛ ዕድሜው እስኪፈጸም ድረስ ያርፍ ዘንድ ከእርሱ ጥቂት ዘወር በል። |
አሁንም እንዲህ እላለሁ፤ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብር ከብዙ ሀብትዋ ጋር ይዋረዳል፤ በቍጥርም ጥቂት ይቀራል፤ ክብርዋም አይገኝም።