ኢዮብ 13:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥንቱን ኀይሉ አያስፈራችሁምን? ግርማስ ከእርሱ ዘንድ አይወድቅባችሁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ግርማው አያስደነግጣችሁምን? ክብሩስ አያስፈራችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክብሩስ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አይወድቅባችሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክብሩ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አያስደነግጣችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክብሩስ አያስፈራችሁምን? ግርማውስ አይወድቅባችሁምን? |
ፍርሀትና ድንጋጤ ወደቀባቸው፤ የክንድህ ብርታትም ከድንጋይ ይልቅ ጸና፤ አቤቱ፥ ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፥ የተቤዠሃቸው እኒህ ሕዝብህ እስኪያልፉ ድረስ፤
እግዚአብሔር ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቍጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን አይችሉም።
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢትረፈረፍና ቢጮኽ ከእርሱ አያልፍም።