እርሱ በተወሰነው ዕድሜ በሌሎች እንዲወድቅ፥ ቤቱም በኃጥኣን እንዲፈርስ ተዘጋጅቶአል። ነገር ግን ማንም ክፉ ሆኖ ንጹሕ እንደሚሆን አይመን።
ኢዮብ 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን የሚያስቈጡትን ሰዎች፥ እርሱ የሚመረምራቸው አይደለምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀማኞች ድንኳን አይታወክም፤ አምላካቸውን በእጃቸው ይዘው እየዞሩም፣ እግዚአብሔርንም እያስቈጡ በሰላም ይኖራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀማኞች ድንኳን በደኅንነት ይኖራል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ ተዝናንተው ተቀምጠዋል፥ እግዚአብሔር ሁሉን በእጃቸው አምጥቶላቸዋል።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይላቸውን እንደ አምላክ አድርገው የሚቈጥሩ ሌቦችና እግዚአብሔርን የካዱ ሰዎች እንኳ በሰላም ይኖራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀማኞች ድንኳን በደኅንነት ይኖራል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ ተዘልለው ተቀምጠዋል፥ እግዚአብሔር ሁሉን በእጃቸው አምጥቶላቸዋል። |
እርሱ በተወሰነው ዕድሜ በሌሎች እንዲወድቅ፥ ቤቱም በኃጥኣን እንዲፈርስ ተዘጋጅቶአል። ነገር ግን ማንም ክፉ ሆኖ ንጹሕ እንደሚሆን አይመን።
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኀጢአተኞች መንገድ ስለ ምን ይቀናል? በደልንስ የሚያደርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላቸዋል?