እንዳልነበረስ ለምን አልሆንሁም? ከማኅፀንም ወደ መቃብር ለምን አልወረድሁም?
ምነው ባልተፈጠርሁ! ወይም ከማሕፀን ቀጥታ ወደ መቃብር በወረድሁ!
እንዳልነበረ በሆንሁ፥ ከማኅፀንም ወደ መቃብር በወሰዱኝ።
ሳልፈጠር በቀረሁ፥ ከማሕፀንም በቀጥታ ወደ መቃብር ብወሰድ ኖሮ በተሻለኝ ነበር።
“ስለ ምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዐይንም ሳያየኝ ለምን አልሞትሁም?
የሕይወቴ ዘመን አጭር አይደለምን? ጥቂት አርፍ ዘንድ ተወኝ፤
ጨለማም እንደሚመጣብኝ፥ ድቅድቁም ጨለማ ፊቴን እንደሚከድን አላወቅሁም።
በማኅፀን ሳለሁ ስለ ምን አልሞትሁም? ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ወዲያውኑ ስለ ምን አልጠፋሁም?
ወይም ከእናቱ ማኅፀን እንደ ወጣ ጭንጋፍ፥ ብርሃንም እንዳላዩ ሕፃናት በሆንሁ ነበር።
የምትሰማቸው አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛቡንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ፥
እናቴ መቃብር ትሆነኝ ዘንድ፥ ማኅፀንዋም ዘወትር ይዞኝ ያቈይ ዘንድ በማኅፀን ውስጥ አልገደለኝምና።