አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፥ “ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።”
ኢዮብ 1:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ ድንገት መጥቶ ቤቱን በአራት ማዕዘኑ መታው፥ ቤቱም በብላቴኖቹ ላይ ወደቀ፥ እነርሱም ሞቱ፤ እኔም ብቻዬን አምልጬ እነግርህ ዘንድ መጣሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ ታላቅ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ መጣ፤ የቤቱንም አራት ማእዘናት መታ፤ እርሱም በልጆቹ ላይ ወድቆ ገደላቸው። እኔም ብቻዬን አመለጥሁ፤ ልነግርህም መጣሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፥ ብርቱ ነፋስ ከምድረበዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከበረሓ የተነሣ ዐውሎ ነፋስ በድንገት መጥቶ ቤቱን በሙሉ በገለባበጠው ጊዜ ቤቱ በላያቸው ላይ ስለ ተደረመሰ ሞቱ፤ እኔ ብቻ አምልጬ የሆነውን ነገር ልነግርህ መጣሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ዐውሎ ነፋስ ከምድረ በዳ መጥቶ የቤቱን አራቱን ማዕዘን መታው፥ በብላቴኖቹም ላይ ወደቀ፥ ሞቱም፥ እኔም እነግርህ ዘንድ ብቻዬን አመለጥሁ አለው። |
አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፥ “ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።”
ንጉሡም እጅግ ደነገጠ፤ በበሩም ላይ ወዳለችው ሰገነት ወጥቶ አለቀሰ፤ ሲሄድም፥ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ ልጄ፥ ልጄ አቤሴሎም ሆይ፥ በአንተ ፋንታ እኔ እንድሞት ቤዛህም እንድሆን ማን ባደረገኝ፥ ልጄ አቤሴሎም፥ ልጄ ሆይ፥” ይል ነበር።
እርሱም ገና ይህን ሲናገር አራተኛው መልእክተኛ መጥቶ ለኢዮብ እንዲህ አለው፥ “ወንዶችና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ሲበሉና የወይን ጠጅ ሲጠጡ፥
አረማውያንም እፉኝቱ በጳውሎስ እጅ ላይ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ሰው ነፍሰ ገዳይ ይመስላል፤ ከባሕር እንኳ በደኅና ቢወጣም በሕይወት ይኖር ዘንድ የእግዚአብሔር ፍርድ አልተወውም” አሉ።
ይኸውም ቀድሞ በዚህ ዓለም ሥርዐት፥ አሁን በከሓድያን ልጆች የሚበረታታባቸውና፥ በነፋስ አምሳል የሚገዛቸው አለቃ እንደ ነበረው ፈቃድ ጸንታችሁ የነበራችሁበት ነው።
ሶምሶንም፥ “ከፍልስጥኤማውያን ጋር ነፍሴ ትውጣ” አለ፤ ተጎንብሶም ምሰሶዎቹን በሙሉ ኀይሉ ገፋቸው፤ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመሳፍንቱ፥ በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ፤ በሞቱም የገደላቸው ሙታን በሕይወቱ ሳለ ከገደላቸው በዙ።