ኤርምያስ 6:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጕድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋቷ ከእርስዋ ዘንድ ይፈልቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእርስዋ ዘንድ ይሰማል፤ ደዌና ቍስልም ሁልጊዜ በፊቷ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የውሃ ጕድጓድ ውሃ እንደሚያመነጭ፣ እርሷም እንዲሁ ክፋቷን ታፈልቃለች። ዐመፅና ጥፋት በውስጧ ይስተጋባል፤ ሕመሟና ቍስሏ ዘወትር ይታየኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጉድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋትዋ ከእርሷ ውስጥ ይፈልቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእርሷ መካከል ይሰማል፥ ደዌና ቁስልም ሁልጊዜ በፊቴ አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጒድጓድ ውሃን እንደሚያፈልቅ፥ ኢየሩሳሌምም የክፋት ሁሉ መፍለቂያ ናት፤ በእርስዋ የሚሰማው የግፍና የጥፋት ጩኸት ብቻ ነው፤ ዘወትር የሚታይባትም ሕመምና ቊስል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጕድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋትዋ ከእርስዋ ዘንድ ይፈልቃል፥ ግፍና ቅሚያ በእርስዋ ዘንድ ይሰማል፥ ደዌና ቍስልም ሁልጊዜ በፊቴ አለ። |
ከእግር ጫማ አንሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም፤ ቍስልና እበጥ የሚመግልም ነው፤ አልፈረጠም፤ አልተጠገነምም፤ በዘይትም አልለዘበም።
ቍስልህ የማይፈወስ ሆኖአልና ስለ ስብራትህ ለምን ትጮኻለህ? በደልህ ታላቅ ስለ ሆነ፥ ኀጢአትህም ስለ በዛ፥ ይህን አድርጌብሃለሁ።
በተገደሉት ኀጢአተኞች አንገት ላይ ያኖሩህ ዘንድ ከንቱ ራእይን ሲያዩልህ፥ በሐሰት ምዋርትም ሲናገሩልህ፥ በኀጢአታቸው ቀጠሮ ጊዜ ቀናቸው ደረሰ።
ደምዋም በመካከልዋ አለ። በተራቈተ ድንጋይ ላይ አደረገችው እንጂ በአፈር ይከደን ዘንድ በመሬት ላይ አላፈሰሰችውም።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእስራኤል አለቆች ሆይ! ይብቃችሁ፤ ግፍንና ዐመፅን አስወግዱ፤ ፍርድንና ጽድቅንም አድርጉ፤ ቅሚያችሁን ከሕዝቤ ላይ አርቁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።