ኤርምያስ 6:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቅምጥል የጽዮን ልጅ ሆይ! ውበትሽ ይጐሳቈላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ውብና ሽሙንሙን የሆነችዋን፣ የጽዮንን ሴት ልጅ አጠፋታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የተዋበችውንና የተቀማጠለችውን የጽዮንን ልጅ አጐሳቁላለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውብና አስደሳች የሆነችው የጽዮን ከተማ ትጠፋለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተዋበችውንና የተሰባቀለችውን የጽዮንን ልጅ አጐሰቍላለሁ። |
እንደምታምጥ፥ የበኵር ልጅዋንም እንደምትወልድ ሴት ጩኸት፥ ጩኸትሽን ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ሰለለ፤ እጆችዋንም ትዘረጋለች፤ ተገድለው ከሞቱት የተነሣ ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ! አለች።
አሌፍ። እግዚአብሔር በቍጣው መቅሠፍት የጽዮንን ሴት ልጅ ምንኛ አጠቈራት! የእስራኤልን ክብር ከሰማይ ወደ ምድር ጣለ፤ በቍጣውም ቀን የእግሩን መረገጫ አላሰበም።
ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድንሻል? ማንስ ያጽናናሻል? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው?
በአንተ ዘንድ የተለሳለሰችና የተቀማጠለች፥ ከልስላሴና ከቅምጥልነት የተነሣ የእግር ጫማዋን በምድር ላይ ያላደረገችው ሴት፥ አቅፋ በተኛችው ባልዋ፥ በወንድና በሴት ልጅዋም ትቀናለች፥