ከባቢሎን ውጡ፤ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፥ “እግዚአብሔር ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል” በሉ።
ኤርምያስ 50:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፤ በበጎችም ፊት እንደ እባቦች ሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከባቢሎን ሽሹ፤ የባቢሎናውያንን ምድር ልቀቁ፤ መንጋ እንደሚመራ የፍየል አውራ ሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከባቢሎን መካከል ሽሹ፥ ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፥ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከባቢሎን ሸሽታችሁ ውጡ! አገሪቱን ለቃችሁ ሂዱ! መንጋውን እንደሚመራ የፍየል አውራ ሁኑ! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከባቢሎን መካከል ሽሹ፥ ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፥ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ። |
ከባቢሎን ውጡ፤ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፥ “እግዚአብሔር ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል” በሉ።
ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይልሽን ልበሺ፤ አንቺም ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያልፍምና ክብርሽን ልበሺ።
እናንተ የእግዚአብሔርን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩስን ነገር አትንኩ፤ ከመካከልዋ ውጡ፤ ራሳችሁን ለዩ።
ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፤ የእግዚአብሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እርሱም ብድራቷን ይከፍላታልና።
በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፣ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።
ማኅበሩንም፥ “ከእነዚህ ክፉዎች ሰዎች ድንኳን ፈቀቅ በሉ፤ በኀጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ ለእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ” ብሎ ተናገራቸው።
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።