Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 50:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከባቢሎን መካከል ሽሹ፥ ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፥ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ከባቢሎን ሽሹ፤ የባቢሎናውያንን ምድር ልቀቁ፤ መንጋ እንደሚመራ የፍየል አውራ ሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከባቢሎን ሸሽታችሁ ውጡ! አገሪቱን ለቃችሁ ሂዱ! መንጋውን እንደሚመራ የፍየል አውራ ሁኑ!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከባ​ቢ​ሎን መካ​ከል ሽሹ፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ውጡ፤ በበ​ጎ​ችም ፊት እንደ እባ​ቦች ሁኑ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከባቢሎን መካከል ሽሹ፥ ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፥ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 50:8
11 Referencias Cruzadas  

ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ፥ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፥ የጌታ የበቀል ጊዜ በእርሷ ላይ ነውና፥ እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታልና።


ከባቢሎን ውጡ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፥ ይህንንም ንገሩ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩ፦ “ጌታ ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል!” በሉ።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርሷ ዘንድ ውጡ፤


ሕዝቤ ሆይ! ከመካከልዋ ውጡ እያንዳንዱም ሰው ከጌታ ጽኑ ቁጣ ነፍሱን ያድን።


ስለዚህም ጌታ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ፤ ርኩስንም አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥


ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ።


በእንስቶች መካከል በድፍረት የሚራመድ አውራ ዶሮ፥ መንጋን የሚመራ አውራ ፍየል፥ በሕዝብ ፊት በግልጥ የሚናገር ንጉሥ።


እርሱም ለማኅበሩ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እባካችሁ፥ ከእነዚህ ክፉዎች ድንኳን ርቃችሁ ገለል በሉ፤ በኃጢአታቸውም ሁሉ እንዳትጠፉ የእነርሱ የሆነውን ሁሉ አትንኩ።”


እናንተ የጌታን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ፥ እልፍ በሉ፥ ከዚያ ውጡ፥ ርኩስን ነገር አትንኩ፥ ከመካከልዋ ውጡ፥ ንጹሐን ሁኑ።


አንቺ ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ጽዮን ሆይ፥ ተነሽ፥ ኰብልይ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios