ኤርምያስ 5:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ፥ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፤ በዚህም ከብረዋል ባለጸጎችም ሆነዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወፎች እንደ ሞሉት ጐጆ፣ ቤታቸው በማጭበርበር የተሞላ ነው፤ ባለጠጎችና ኀያላን ሆነዋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወፍ እንደሞላበት የወፍ ቀፎ፥ እንዲሁ ቤቶቻቸው በሽንገላ ተሞልቶአል፤ ስለዚህም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዳኝ ወፎችን ይዞ በወፎች ጎጆ እንደሚያሰፍር፥ እነርሱም ቤታቸውን ከብዝበዛ ባገኙት ሀብት ይሞላሉ፤ ብርቱዎችና ሀብታሞች የሆኑትም ስለዚህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ፥ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፥ እንዲሁም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል። |
እግዚአብሔር ከሕዝቡ ሽማግሌዎችና ከአለቆቻቸው ጋር ለፍርድ ይመጣል፤ እንዲህም ይላል፥ “ወይኔን አቃጥላችኋል፤ ከድሃው የበዘበዛችሁትም በቤታችሁ አለ፤
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኀጢአተኞች መንገድ ስለ ምን ይቀናል? በደልንስ የሚያደርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላቸዋል?
አራጣንም በአራጣ ላይ ይቀበላሉ፤ ተንኰልን በተንኰል ላይ ይሠራሉ፤ “እኔንም ያውቁኝ ዘንድ እንቢ ብለዋል፥” ይላል እግዚአብሔር።
ኤፍሬምም፥ “ባለጸጋ ሆኜአለሁ፤ ሀብትንም አግኝቻለሁ፤ በድካሜም ሁሉ ኀጢአት የሚሆን በደል አይገኝብኝም” አለ።
በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤