በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፥ ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
ኤርምያስ 5:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከንፈራቸውም እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ ሁሉም ኀያላን ናቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፍላጻቸው ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ ሁሉም ብርቱ ተዋጊዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ ሁሉም ኃያላን ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀስተኞቻቸው ያለ ምሕረት የሚገድሉ ኀይለኞች ጦረኞች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የፍላጻቸውም ሰገባ እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ ሁሉም ኃያላን ናቸው። |
በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፥ ጕሮሮኣቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።
ፍላጾቻቸው ተስለዋል፤ ቀስቶቻቸውም ሁሉ ተለጥጠዋል፤ የፈረሶቻቸውም ኮቴ እንደ ቡላድ፥ የሰረገሎቻቸውም መንኰራኵር እንደ ዐውሎ ነፋስ ይቈጠራል።
ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተምማል፤ በሰረገላና በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠፉሻል።