የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ የጻድቁን ድንቅ ተስፋ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እነርሱ ግን፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ ለሚያፈርሱ ወንጀለኞች ወዮላቸው!” አሉ።
ኤርምያስ 5:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወንጅለዋል” ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት፣ ፈጽመው ከድተውኛል፤” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ አታለዋል ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ፈጽሞ ከድተውኛል፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤል ቤትና የይሁዳ ቤት በእኔ ላይ እጅግ ወንጅለዋል ይላል እግዚአብሔር። |
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ የጻድቁን ድንቅ ተስፋ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እነርሱ ግን፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ ለሚያፈርሱ ወንጀለኞች ወዮላቸው!” አሉ።
አላወቅህም፤ አላስተዋልህም፤ ጆሮህን ከጥንት አልከፈትሁልህም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ፥ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ ዐውቄአለሁና።
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኀጢአተኞች መንገድ ስለ ምን ይቀናል? በደልንስ የሚያደርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላቸዋል?
“ወደ ቅጥርዋ ወጥታችሁ አፍርሱ፤ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፤ የእግዚአብሔር ናቸውና መጠጊያዎችዋን አትርፉ።
ሁሉም አመንዝሮች፥ የዐመጸኞች ጉባኤ ናቸውና ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ ማደሪያን ማን በሰጠኝ?
ዲቃሎችን ልጆች ወልደዋልና እግዚአብሔርን ከድተዋል፤ አሁንም ኵብኵባ እነርሱንና ርስታቸውን ይበላቸዋል።