La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 49:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰም​ቻ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛብ ሀገ​ሮች ተሰ​ብ​ሰቡ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ኑ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ውጓት፥ የሚል መል​እ​ክ​ተኛ ተል​ኳል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤ “እርሷን ለመውጋት ተሰብሰቡ፤ ለጦርነትም ውጡ” የሚል መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኳል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከጌታ ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ “ተሰብሰቡ፥ በእርሷም ላይ ኑ ለጦርነትም ተነሡ” የሚል መልእክተኛ ተልኮአል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንድ መልእክት ከእግዚአብሔር ሰምቼአለሁ፤ “በኤዶም ሕዝብ ላይ አደጋ ለመጣል ተሰብሰቡ! ለጦርነትም ተነሡ!” ብሎ የሚናገር መልእክተኛ ወደ ሕዝቦች ተልኮአል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ ተሰብሰቡ፥ በእርስዋም ላይ ኑ ለሰልፍም ተነሡ የሚል መልእክተኛ ተልኮአል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 49:14
12 Referencias Cruzadas  

አለ​ቆች ምንም በጣ​ኔ​ዎስ ቢሆኑ፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ምንም ወደ ሓኔስ ቢደ​ርሱ፥


እነሆ፥ መን​ፈ​ስን በላዩ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ወሬ​ንም ይሰ​ማል፤ ወደ ምድ​ሩም ይመ​ለ​ሳል፤ በም​ድ​ሩም በሰ​ይፍ እን​ዲ​ወ​ድቅ አደ​ር​ጋ​ለሁ በሉት” አላ​ቸው።


እነሆ በሕ​ዝብ ዘንድ የተ​ጠ​ቃህ፥ በሰ​ዎ​ችም ዘንድ የተ​ና​ቅህ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ።


“ፍላ​ጾ​ችን አዘ​ጋጁ፤ ጕራ​ን​ጕ​ሬ​ዎ​ች​ንም ሙሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያጠ​ፋት ዘንድ ቍጣው በባ​ቢ​ሎን ላይ ነውና የሜ​ዶ​ንን ንጉሥ መን​ፈስ አስ​ነ​ሥ​ቶ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል የመ​ቅ​ደሱ በቀል ነውና።


በም​ድ​ርም ከሚ​ሰማ ወሬ የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ ልባ​ች​ሁም የዛለ አይ​ሁን፤ በአ​ንድ ዓመት ወሬ ይመ​ጣል፤ ከዚ​ያም በኋላ በሌ​ላው ዓመት ወሬ ይመ​ጣል፤ በም​ድ​ርም ላይ ግፍ ይነ​ግ​ሣል፤ አለ​ቃም በአ​ለቃ ላይ ይነ​ሣል።


ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው።