La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 48:39 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዴት ተለ​ወ​ጠች! ከእ​ፍ​ረ​ትም የተ​ነሣ ሞአብ ጀር​ባ​ዋን እን​ዴት መለ​ሰች! ሞአ​ብም በዙ​ሪ​ያዋ ላሉት ሁሉ መሳ​ቂ​ያና መሳ​ለ​ቂያ ትሆ​ና​ለች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ! ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ! ሞዓብ የመሰደቢያ፣ በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዴት ተሰበረ! እንዴትስ አለቀሱ! በእፍረትም የተነሣ ሞዓብ ጀርባውን እንዴት ሰጠ! ስለዚህ ሞዓብ በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና መደንገጫ ሆኖአል።”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሞአብ ላይ ምን ዐይነት አስደንጋጭ ሁናቴ ደርሶ ነው የምታለቅሰው? እንዴትስ በዕፍረት ጀርባዋን ትሰጣለች? ስለዚህም ለጐረቤቶችዋ ሁሉ መሳለቂያና አስደንጋጭ ሆናለች።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዴት ተገለበጠ! በእፍረትም የተነሣ ሞዓብ ጀርባውን እንዴት መለሰ! ብላችሁ አልቅሱ። ሞዓብም በዙሪያው ላሉት ሁሉ መሳቂያና ድንጋጤ ይሆናል።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 48:39
10 Referencias Cruzadas  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ይታ​መ​ን​ባት ከነ​በ​ረው ከቤ​ቴል እን​ዳ​ፈረ፥ እን​ዲሁ ሞአብ ከካ​ሞሽ ታፍ​ራ​ለች።


በዙ​ሪ​ያው ያላ​ችሁ ሁሉ ስሙ​ንም የም​ታ​ውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠን​ካ​ራ​ውም ሽመል፥ እን​ዴት ተሰ​በረ! ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሱ​ለት።


አሌፍ። ሕዝብ ሞል​ቶ​ባት የነ​በ​ረች ከተማ ብቻ​ዋን እን​ዴት ተቀ​መ​ጠች! በአ​ሕ​ዛብ ተመ​ልታ የነ​በ​ረች እንደ መበ​ለት ሆና​ለች፤ አሕ​ዛ​ብን ትገዛ የነ​በ​ረች፥ አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ንም ትገዛ የነ​በ​ረች ገባር ሆና​ለች።


አሌፍ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው መቅ​ሠ​ፍት የጽ​ዮ​ንን ሴት ልጅ ምንኛ አጠ​ቈ​ራት! የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ክብር ከሰ​ማይ ወደ ምድር ጣለ፤ በቍ​ጣ​ውም ቀን የእ​ግ​ሩን መረ​ገጫ አላ​ሰ​በም።


አሌፍ። ወርቁ እን​ዴት ደበሰ! ጥሩው ብር እን​ዴት ተለ​ወጠ! የከ​በ​ረው ዕንቍ በጎ​ዳ​ናው ሁሉ እን​ዴት ተበ​ተነ!