በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ እስከ ሴዴቅያስ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።
ኤርምያስ 39:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሴዴቅያስም በዐሥራ አንደኛው ዓመተ መንግሥት በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን ከተማዪቱ ተለያየች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሴዴቅያስ ዘመነ መንግሥት በዐሥራ አንደኛው ዓመት በአራተኛው ወር፣ በወሩም በዘጠነኛው ቀን የከተማዪቱ ቅጥር ተሰበረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሴዴቅያስም በዓሥራ አንደኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በዘጠነኛው ቀን የከተማይቱ ቅጥር ተጣሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴዴቅያስ በነገሠ በዐሥራ አንደኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ በዘጠነኛው ቀን የከተማይቱ ቅጽሮች ተጣሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሴዴቅያስም በአሥራ አንደኛው ዓመት በአራተኛው ወር ከወሩም በዘጠነኛው ቀን ከተማይቱ ተሰበረች። |
በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ እስከ ሴዴቅያስ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።
በይሁዳ ንጉሥ በሴዴቅያስ በዐሥረኛው ዓመተ መንግሥት፥ በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር በዐሥራ ስምንተኛው ዓመተ መንግሥት ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደ ኤርምያስ የመጣው ቃል ይህ ነው።
እነሆ እኔ አዝዛለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ወደዚህችም ሀገር እመልሳቸዋለሁ፤ እርስዋንም ይወጋሉ፤ ይይዙአትማል፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው የሌለበት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።”
“ወደ ቅጥርዋ ወጥታችሁ አፍርሱ፤ ነገር ግን ፈጽማችሁ አታጥፉ፤ የእግዚአብሔር ናቸውና መጠጊያዎችዋን አትርፉ።
እንዲህም ሆነ፤ በተማረክን በዐሥራ ሁለተኛው ዓመት በዐሥረኛው ወር ከወሩም በአምስተኛው ቀን ከኢየሩሳሌም ያመለጠ አንድ ሰው ወደ እኔ መጥቶ፦ ከተማዪቱ ተያዘች አለኝ።
የብረት ምጣድም ወስደህ በአንተና በከተማዪቱ መካከል ለብረት ቅጥር አድርገው፤ ፊትህንም ወደ እርስዋ አቅና፤ የተከበበችም ትሆናለች፤ አንተም ትከብባታለህ። ይህም ለእስራኤል ልጆች ምልክት ይሆናል።
የእስራትህም ወራት በተፈጸመ ጊዜ በከተማዪቱ መካከል ሢሶውን በእሳት ታቃጥላለህ፤ ሢሶውንም ወስደህ ዙሪያውን በጎራዴ ትመታለህ፤ ሢሶውንም ወደ ነፋስ ትበትናለህ፤ እኔም በኋላቸው ጎራዴ እመዝዛለሁ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአራተኛው ወር ጾም የአምስተኛውም የሰባተኛውም የአሥረኛውም ወር ጾም ለይሁዳ ቤት ደስታና ተድላ የሐሤትም በዓላት ይሆናል፣ ስለዚህም እውነትንና ሰላምን ውደዱ።