ነገር ግን እናንተን የሚወጉትን የከለዳውያንን ጭፍራ ሁሉ ብትመቱ፤ ከእነርሱም ጥቂት ተወግተው ያልሞቱ ቢቀሩ ሁሉ እያንዳንዱ በስፍራው ይነሣሉ፤ ይህቺንም ሀገር በእሳት ያቃጥላሉ።”
ኤርምያስ 37:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከለዳውያንም ሠራዊት ከፈርዖን ሠራዊት ፊት የተነሣ ከኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ እንዲህ ሆነ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባቢሎን ሰራዊት ከፈርዖን ጭፍራ የተነሣ ከኢየሩሳሌም ከወጣ በኋላ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፈርዖንም ሠራዊት ከመቃረቡ የተነሣ የከለዳውያን ሠራዊት ከኢየሩሳሌም ተመልሶ በነበረ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የግብጽ ሠራዊት መቃረቡ እንደ ተሰማ የባቢሎን ሠራዊት ወደ ኋላ አፈግፍጎ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከለዳውያንም ሠራዊት ከፈርዖን ሠራዊት ፊት የተነሣ ከኢየሩሳሌም በተመለሰ ጊዜ፥ |
ነገር ግን እናንተን የሚወጉትን የከለዳውያንን ጭፍራ ሁሉ ብትመቱ፤ ከእነርሱም ጥቂት ተወግተው ያልሞቱ ቢቀሩ ሁሉ እያንዳንዱ በስፍራው ይነሣሉ፤ ይህቺንም ሀገር በእሳት ያቃጥላሉ።”
የፈርዖንም ሠራዊት ከግብፅ ወጣ፤ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬአቸውን በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ።