Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤርምያስ 37:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የፈ​ር​ዖ​ንም ሠራ​ዊት ከግ​ብፅ ወጣ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ከብ​በ​ዋት የነ​በሩ ከለ​ዳ​ው​ያን ይህን ወሬ​አ​ቸ​ውን በሰሙ ጊዜ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተመ​ለሱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የፈርዖንም ሰራዊት ከግብጽ ወጥቶ ነበርና ኢየሩሳሌምን ከብበው የነበሩት ባቢሎናውያን ይህን ሲሰሙ ኢየሩሳሌምን ለቅቀው ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የፈርዖንም ሠራዊት ከግብጽ ወጣ፤ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በዚያን ጊዜ የባቢሎን ሠራዊት ኢየሩሳሌምን ከበበ፤ ነገር ግን የግብጽ ሠራዊት ድንበሩን አልፎ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ወደ ኋላው አፈገፈገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የፈርዖንም ሠራዊት ከግብጽ ወጣ፥ ኢየሩሳሌምንም ከብበዋት የነበሩ ከለዳውያን ይህን ወሬ በሰሙ ጊዜ ከኢየሩሳሌም ተመለሱ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 37:5
7 Referencias Cruzadas  

የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ለግ​ብፅ ንጉሥ የነ​በ​ረ​ውን ሁሉ ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ወስዶ ነበ​ርና የግ​ብፅ ንጉሥ ከዚያ ወዲህ ከሀ​ገሩ አል​ወ​ጣም።


የይ​ሁ​ዳ​ንም ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያ​ስ​ንና መኳ​ን​ን​ቱን ለጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም ለሚ​ሹ​አት እጅ ከእ​ና​ን​ተም ለተ​መ​ለ​ሱት ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ።


የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ሠራ​ዊት ከፈ​ር​ዖን ሠራ​ዊት ፊት የተ​ነሣ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም በተ​መ​ለሰ ጊዜ እን​ዲህ ሆነ፤


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከእኔ ትጠ​ይቁ ዘንድ የላ​ካ​ች​ሁን የይ​ሁ​ዳን ንጉሥ እን​ዲህ በሉት፦ እነሆ ሊረ​ዳ​ችሁ የወ​ጣው የፈ​ር​ዖን ሠራ​ዊት ወደ ሀገሩ ወደ ግብፅ ይመ​ለ​ሳል።


እርሱ ግን በእ​ርሱ ላይ ሸፈተ፤ ፈረ​ሶ​ች​ንና ብዙ​ንም ሕዝብ ይሰ​ጡት ዘንድ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ወደ ግብፅ ላከ። በውኑ ይከ​ና​ወ​ን​ለት ይሆን? ይህ​ንስ ያደ​ረገ ያመ​ል​ጣ​ልን? ቃል ኪዳ​ን​ንስ ያፈ​ረሰ ያመ​ል​ጣ​ልን?


ብዙ​ዎ​ችን ነፍ​ሳት ለማ​ስ​ወ​ገድ ምሽ​ግን በመ​ሸጉ፥ ቅጥ​ር​ንም በሠሩ ጊዜ፥ ፈር​ዖን በታ​ላቅ ኀይ​ልና በብዙ ሕዝብ በጦ​ር​ነት አይ​ረ​ዳ​ውም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos