“አንድ የመጽሐፍ ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን ከይሁዳ ንጉሥ ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት።
ኤርምያስ 36:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባሮክም፥ “ኤርምያስ ይህን ቃል ከአፉ ይነግረኝ ነበር፤ እኔም በመጽሐፉ ላይ እጽፍ ነበር” ብሎ መለሰላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባሮክም፣ “አዎን ይህን ሁሉ በቃሉ ነገረኝ፤ እኔም በብራናው ላይ በቀለም ጻፍሁ” ብሎ መለሰላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባሮክም፦ “እነዚህን ቃላት ከአፉ ይነግረኝ ነበር፥ እኔም በመጽሐፉ ላይ በቀለም እጽፍ ነበር” ብሎ መለሰላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባሮክም “በእርግጥ ቃሉን አንድ በአንድ የነገረኝ ኤርምያስ ነው፤ እኔም በዚህ ብራና ላይ በቀለም ጻፍኩት” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሮክም፦ ይህን ቃል ከአፉ ይነግረኝ ነበር፥ እኔም በመጽሐፉ ላይ በቀለም እጽፍ ነበር ብሎ መለሰላቸው። |
“አንድ የመጽሐፍ ክርታስ ውሰድ፥ ለአንተም ከተናገርሁበት ቀን ከይሁዳ ንጉሥ ከኢዮስያስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤልና በይሁዳ ላይ በአሕዛብም ሁሉ ላይ የተናገርሁህን ቃል ሁሉ ጻፍበት።
ንጉሡም፥ ባሮክ ከኤርምያስ አፍ የጻፈው ቃል ያለበትን ክርታስ ካቃጠለ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል መጣ፦
ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ፤ ለኔርዩም ልጅ ለጸሓፊው ለባሮክ ሰጠው፤ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ጻፈበት፤ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨመረበት።
ኤርምያስም የኔርዩን ልጅ ባሮክን ጠራ፤ ባሮክም እግዚአብሔር ለእርሱ የተናገረውን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ በመጽሐፉ ክርታስ ጻፈ።
በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም በአራተኛው ዓመተ መንግሥት እነዚህን ቃላት ከኤርምያስ አፍ በመጽሐፍ በጻፋቸው ጊዜ፥ ነቢዩ ኤርምያስ ለኔርዩ ልጅ ለባሮክ የተናገረው ቃል ይህ ነው።