ኤርምያስ 36:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፦ ቃሉን ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈርተው እርስ በርሳቸው ተመካከሩ፤ ባሮክንም፥ “ይህን ቃል ሁሉ በርግጥ ለንጉሡ እንናገራለን” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ቃሉን ሁሉ በሰሙ ጊዜ እርስ በርሳቸው በፍርሀት በመተያየት ባሮክን፣ “ይህን ሁሉ ቃል ለንጉሡ መንገር ይገባናል።” አሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃሎቹንም ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈርተው እርስ በእርሳቸው ተያዩ፥ ባሮክንም፦ “እነዚህን ቃላት ሁሉ በእርግጥ ለንጉሡ እንናገራለን” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንብቦ ከጨረሰም በኋላ ከመደንገጣቸው የተነሣ እርስ በርሳቸው ተያይተው ባሮክን “ይህን ጉዳይ ለንጉሡ ማስታወቅ አለብን” አሉት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃሉንም ሁሉ በሰሙ ጊዜ ፈርተው እርስ በእርሳቸው ተመካከሩ፥ ባሮክንም፦ ይህን ቃል ሁሉ በእርግጥ ለንጉሡ እንናገራለን አሉት። |
ለነገሥታቱና ለመኳንንቱ፦ የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ራሳችሁን አዋርዳችሁ ተቀመጡ በላቸው።
ስለ ነቢያት ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል፤ አጥንቶችም ሁሉ ታውከዋል፤ ከእግዚአብሔር ፊት የተነሣ፤ ከጌትነቱም ክብር የተነሣ እኔም በመከራ እንደ ተቀጠቀጠ ሰው፥ የወይን ጠጅ እንዳሸነፈውም እንደ ሰካራም ሰው ሆኛለሁ።