ሚክያስም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይ ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው፤ ቆመው አየሁ።”
ኤርምያስ 34:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነገር ግን የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ በሰይፍ አትሞትም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ነገር ግን፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፤ በሰይፍ አትሞትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን፥ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ! የጌታን ቃል ስማ፤ ጌታ ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ ‘በሰይፍ አትሞትም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሴዴቅያስ ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ የምለውን ስማ፤ በጦርነት ላይ አትሞትም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን፥ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፥ እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ በሰይፍ አትሞትም፥ በሰላም ትሞታለህ እንጂ፥ |
ሚክያስም አለ፥ “እንዲህ አይደለም፤ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይ ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው፤ ቆመው አየሁ።”
ሴዴቅያስም ወደ ባቢሎን ይገባል፤ እኔም እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይኖራል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ከከለዳውያን ጋር ብቷጉ ምንም አይቀናችሁም።”
አንተም በርግጥ ትያዛለህ፤ በእጁም አልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም፤ ዐይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዐይን ታያለች፤ እርሱም ከአንተ ጋር አፍ ለአፍ ይናገራል፤ ወደ ባቢሎንም ትገባለህ።
ነገር ግን በሰላም ትሞታለህ፥ ከአንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገሥታት አባቶችህ እሳት ይቃጠልላቸው እንደ ነበር እንዲሁ ያቃጥሉልሃልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ! እያሉ ያለቅሱልሃል፤ እኔ ቃልን ተናግሬአለሁና” ይላል እግዚአብሔር።
“በእግዚአብሔር ቤት በር ቁም፤ ይህንም ቃል እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ለእግዚአብሔር ትሰግዱ ዘንድ በእነዚህ በሮች የምትገቡ ከይሁዳ ያላችሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ምሕረት፥ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚኖሩትን ይወቅሳልና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።