እንደ ንጉሡም ትእዛዝ መልእክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የአለቆቹን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ፈጥነው ሄዱ፥ “የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ወዳመለጠ ቅሬታችሁ እንዲመለስ ወደ አብርሃምና ወደ ይስሐቅ ወደ ያዕቆብም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።
ኤርምያስ 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዳተኞች ልጆች ሆይ! እኔ እገዛችኋለሁና ተመለሱ፤ ይላል እግዚአብሔር። አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ፤ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከዳተኛ ልጆች ሆይ፤ እኔ ባለቤታችሁ ነኝና ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድ ሁለት መርጫችሁ ወደ ጽዮን አመጣችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዳተኞች ልጆች ሆይ! እኔ ጌታችሁ ነኝና ተመለሱ ይላል ጌታ፤ አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ፥ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ፤” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እናንተ እምነት የማይጣልባችሁ ሕዝብ ሆይ! የእኔ ስለ ሆናችሁ ተመለሱ፤ ከእናንተ መካከል ከየአንዳንዱ ከተማ አንዳንድ፥ ከእያንዳንዱም ቤተሰብ ሁለት ሁለት መርጬ ወደ ጽዮን ተራራ አመጣችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዳተኞች ልጆች ሆይ፥ እኔ ባላችሁ ነኝና ተመለሱ ይላል እግዚአብሔር፥ አንዱንም ከአንዲት ከተማ ሁለቱንም ከአንድ ወገን እወስዳችኋለሁ፥ ወደ ጽዮንም አመጣችኋለሁ፥ |
እንደ ንጉሡም ትእዛዝ መልእክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የአለቆቹን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ፈጥነው ሄዱ፥ “የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ወዳመለጠ ቅሬታችሁ እንዲመለስ ወደ አብርሃምና ወደ ይስሐቅ ወደ ያዕቆብም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ።
ወይራ በተመታ ጊዜ ሁለት ወይም ሦስት ፍሬ በራሱ ላይ እንደሚቀር፥ አራት ወይም አምስት በዛፊቱ ጫፍ እንደሚገኝ፥ በእርሱ ዘንድ ቃርሚያ ይቀራል” ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር።
በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ፈሳሽ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ዐጥር ያጥራል፤ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
ፈጣሪሽ እግዚአብሔር ነው፤ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው፤ የእስራኤልም አምላክ ታዳጊሽ ነው፤ እርሱም በምድር ሁሉ እንደዚሁ ይጠራል።
ክፉ ሰው መንገዱን፥ በደለኛም ዐሳቡን ይተው፤ ወደ እግዚአብሔርም ይመለስ፤ እርሱም ይምረዋል፤ እርሱ ብዙ በደላችሁን ይተውላችኋልና።
በእርስዋም ዘንድ ዐሥረኛ እጅ ቀርቶ እንደ ሆነ እርሱ ደግሞ ይቃጠላል፤ ቅጠሎቻቸውም በረገፉ ጊዜ እንደ ግራርና እንደ ኮምበል ዛፍ ሁነው ይቀራሉ።
ክፋትሽ ይገሥጽሻል፤ ክዳትሽም ይዘልፍሻል፤ እኔን መተውሽም ክፉና መራራ ነገር መሆኑን ታውቂያለሽ፤ ትረጂማለሽ” ይላል አምላክሽ እግዚአብሔር፤ “መፈራቴም በአንቺ ዘንድ የለም፤ ይህም ደስ አላሰኘኝም” ይላል አምላክሽ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
“ሂድ፤ እንዲህ ብለህ በኢየሩሳሌም ጆሮ ተናገር፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ምሕረት፥ የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስቤአለሁ።
የሕዝቤን ቅሬታ ከበተንኋቸው ምድር ሁሉ ወደ መሰማሪያቸው ሰብስቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ይበዛሉ፤ ይባዛሉም።
እገለጥላችኋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ምርኮአችሁንም እመልሳለሁ፤ ከአሕዛብ ሁሉ ዘንድ እናንተንም ከበተንሁበት ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ እናንተንም ለምርኮ ወዳፈለስሁበት ስፍራ እመልሳችኋለሁ።
“ሰው ሚስቱን ቢፈታ፥ ከእርሱም ዘንድ ሄዳ ሌላ ወንድ ብታገባ፥ በውኑ ደግሞ ወደ እርሱ ትመለሳለችን? ያች ሴት እጅግ የረከሰች አይደለችምን? አንቺም ከብዙ እረኞች ጋር አመንዝረሻል፤ ወደ እኔም ትመለሻለሽን? ይላል እግዚአብሔር።
ሂድና ይህን ቃል ወደ ሰሜን ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ከዳተኛዪቱ እስራኤል ሆይ! ወደ እኔ ተመለሽ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ መሓሪ ነኝና፥ ለዘለዓለምም አልቈጣምና በእናንተ ላይ ፊቴን አላጸናም፥” ይላል እግዚአብሔር።
ከዳተኛዪቱም እስራኤል እንዳመነዘረች አየሁ፤ የፍችዋንም ደብዳቤ በእጅዋ ሰጥቼ ሰደድኋት፤ ጎስቋላ እኅቷ ይሁዳ ግን በዚያ አልፈራችም፤ እርስዋም ደግሞ ሄዳ አመነዘረች።
ይመጣሉ፤ በጽዮንም ተራራ ደስ ይላቸዋል፤ ወደ እግዚአብሔርም በጎነት፥ ወደ እህልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይትም፥ ወደ በጎችና ወደ ላሞች ሀገርም ይሰበሰባሉ፤ ነፍሳቸውም እንደ ረካች ገነት ትሆናለች፤ ከእንግዲህም ወዲህ አይራቡም።
ከግብፅ ሀገር አወጣቸው ዘንድ እጃቸውን በያዝሁበት ቀን ከአባቶቻቸው ጋር እንደ ገባሁት ያለ ቃል ኪዳን አይደለም፤ እነርሱ በኪዳኔ አልጸኑምና፥ እኔም ቸል አልኋቸው፥ ይላል እግዚአብሔር።
በኤፍሬም ተራሮች ላይ የሚከራከሩ፦ ተነሡ፤ ወደ ጽዮን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ ብለው የሚጠሩባት ቀን ትመጣለችና።”
የቀደሙት ነቢያት ለአባቶቻችሁ እንዲህ ብለው ሰብከዋል፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ሥራችሁ ተመለሱ፣ እነርሱ ግን አልሰሙም፥ እኔንም አላደመጡም፣ እንደ እነርሱ አትሁኑ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ኢሳይያስም ድምፁን ከፍ አድርጎ ስለ እስራኤል እንዲህ አለ፥ “የእስራኤል ልጆች ቍጥራቸው እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም የተረፉት ይድናሉ።