La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 29:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚህ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን የሰ​ደ​ድ​ኋ​ችሁ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።”

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን የሰደድኋችሁ ምርኮኞች ሁሉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ እናንተ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን ያፈለስኋችሁ ምርኮኞች ሁሉ ሆይ! የጌታን ቃል ስሙ፦

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን እንድትሰደዱ ያደረግኋችሁ እናንተም ሁላችሁ እኔ እግዚአብሔር የምለውን ቃል ስሙ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን የሰደድኋችሁ ምርኮኞች ሁሉ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 29:20
8 Referencias Cruzadas  

“የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ደ​ዚህ እንደ መል​ካሙ በለስ፥ እን​ዲሁ ከዚህ ስፍራ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን ምድር የሰ​ደ​ድ​ሁ​ትን የይ​ሁ​ዳን ምርኮ ለበ​ጎ​ነት እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለሁ።


ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ወደ ተረ​ፉት የም​ርኮ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ ወደ ካህ​ና​ቱም፥ ወደ ሐሰ​ተ​ኞች ነቢ​ያ​ቱም፥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ባቢ​ሎን ማርኮ ወዳ​ፈ​ለ​ሰ​ውም ሕዝብ ሁሉ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የላ​ከው የደ​ብ​ዳ​ቤው ቃል ይህ ነው።


ይህም የሆ​ነው ንጉሡ ኢኮ​ን​ያ​ንና እቴ​ጌ​ዪቱ፥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ቹም፥ የይ​ሁ​ዳና የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም አለ​ቆች ነጻ​ዎ​ችና እሥ​ረ​ኞች፥ ብል​ሃ​ተ​ኞ​ችና ብረት ሠራ​ተ​ኞ​ችም ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከወጡ በኋላ ነው።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አሔ​ል​ማ​ዊው ስለ ሸማያ እን​ዲህ ይላል ብለህ ወደ ምር​ኮ​ኞች ሁሉ ላክ፦ እኔ ሳል​ል​ከው ሸማያ ትን​ቢት ተና​ግ​ሮ​ላ​ች​ኋ​ልና፥ በሐ​ሰ​ትም እን​ድ​ት​ታ​መኑ አድ​ር​ጓ​ች​ኋ​ልና።


ከመ​ካ​ከ​ል​ዋም አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በባ​ዕ​ዳ​ንም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ በላ​ያ​ች​ሁም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


ተነ​ሥ​ተ​ህም ወደ ተማ​ረኩ ወደ ወገ​ንህ ልጆች ሂድ፤ እነ​ር​ሱም ቢሰሙ ወይም ቢፈሩ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል ብለህ ንገ​ራ​ቸው” አለኝ።


በቴ​ል​አ​ቢ​ብም ወደ አሉ፥ በኮ​ቦ​ርም ወንዝ አጠ​ገብ ወደ ተቀ​መጡ ምር​ኮ​ኞች መጣሁ፤ በተ​ቀ​መ​ጡ​በ​ትም ቦታ ተቀ​መ​ጥሁ፤ በዚ​ያም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው እየ​ተ​መ​ላ​ለ​ስሁ ሰባት ቀን ተቀ​መ​ጥሁ።


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጠሽ ውለጂ፥ አሁን ከከተማ ትወጫለሽና፥ በሜዳም ትቀመጫለሽ፥ ወደ ባቢሎንም ትደርሻለሽ፥ በዚያም ያድንሻል፥ በዚያም እግዚአብሔር ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።