ኤርምያስ 29:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር በዳዊት ዙፋን ስለ ተቀመጠ ንጉሥ፥ ከእናንተም ጋር ስላልተማረኩት ወንድሞቻችሁ፥ በዚህች ከተማ ስለሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ግን በዳዊት ዙፋን ላይ ስለሚቀመጠው ንጉሥና ከእናንተ ጋራ ተማርኮ ስላልሄደው ወገንህ በዚህ ከተማ ስለ ቀረው ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ይላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዳዊት ዙፋን ላይ ስለ ተቀመጠው ንጉሥ፥ ከእናንተም ጋር ተማርከው ስላልሄዱት ወንድሞቻችሁ፥ በዚህች ከተማ ስለሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ ጌታ እንዲህ ይላልና፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የዳዊትን ዙፋን ወርሶ ገዢ ስለ ሆነው ንጉሥና እንደ እናንተ ተማርከው ስላልተወሰዱት በዚህች ከተማ ስለሚገኙት ዘመዶቻችሁ እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር በዳዊት ዙፋን ስለ ተቀመጠ ንጉሥ ከእናንተም ጋር ስላልተማረኩት ወንድሞቻችሁ፥ በዚህች ከተማ ስለሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ እንዲህ ይላልና፦ |
በአንደኛዪቱ ቅርጫት አስቀድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረባት፤ በሁለተኛዪቱም ቅርጫት ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ በለስ ነበረባት።
እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፥ “ከክፋቱ የተነሣ ይበላ ዘንድ እንደማይቻል እንደ ክፉው በለስ፥ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፤ አለቆቹንም፥ በዚች ሀገር የሚቀሩትንም የኢየሩሳሌምን ቅሬታ፥ በግብጽም ሀገር የሚቀመጡትን እንዲሁ አደርጋቸዋለሁ።
ኤርምያስም የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን እንዲህ ሲል ላከው፦
ስለዚህ ቍጣዬን አፈሰስሁባቸው፤ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።”