Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 29:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በዳዊት ዙፋን ላይ ስለ ተቀመጠው ንጉሥ፥ ከእናንተም ጋር ተማርከው ስላልሄዱት ወንድሞቻችሁ፥ በዚህች ከተማ ስለሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ ጌታ እንዲህ ይላልና፦

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔር ግን በዳዊት ዙፋን ላይ ስለሚቀመጠው ንጉሥና ከእናንተ ጋራ ተማርኮ ስላልሄደው ወገንህ በዚህ ከተማ ስለ ቀረው ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ይላል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የዳዊትን ዙፋን ወርሶ ገዢ ስለ ሆነው ንጉሥና እንደ እናንተ ተማርከው ስላልተወሰዱት በዚህች ከተማ ስለሚገኙት ዘመዶቻችሁ እግዚአብሔር የሚለውን ቃል ስሙ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዳ​ዊት ዙፋን ስለ ተቀ​መጠ ንጉሥ፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ስላ​ል​ተ​ማ​ረ​ኩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ፥ በዚ​ህች ከተማ ስለ​ሚ​ኖሩ ሕዝብ ሁሉ እን​ዲህ ይላ​ልና፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እግዚአብሔር በዳዊት ዙፋን ስለ ተቀመጠ ንጉሥ ከእናንተም ጋር ስላልተማረኩት ወንድሞቻችሁ፥ በዚህች ከተማ ስለሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ፥ እንዲህ ይላልና፦

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 29:16
11 Referencias Cruzadas  

ስለዚህ ቁጣዬን አፈሰስሁባቸው፤ በመዓቴም እሳት አጠፋኋቸው፤ መንገዳቸውንም በራሳቸው ላይ መለስሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ኤርምያስ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር ወደ ባቢሎን በላካቸው በሳፋን ልጅ በኤልዓሣና በኬልቅያስ ልጅ በገማርያ እጅ ደብዳቤውን ላከው፤ እንዲህም የሚል ነበር፦


በአንደኛው ቅርጫት አስቀድሞ እንደ ደረሰ በለስ የሚመስል እጅግ መልካም በለስ ነበረበት፤ በሁለተኛውም ቅርጫት ከክፋቱ የተነሣ ሊበላ የማይችል እጅግ ክፉ በለስ ነበረበት።


ሴዴቅያስ መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አንድ ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ።


“ነገር ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ከክፋቱ የተነሣ ሊበላ እንደማይችል እንደ ክፉው በለስ፥ እንዲሁ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን አለቆቹንም፥ በዚህችም አገር የሚቀሩትን የኢየሩሳሌምን ትሩፍ፥ በግብጽም አገር የሚቀመጡትን ክፉውን አደርግባቸዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios