ኤርምያስ 26:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን፥ እነሆ በእጃችሁ ነኝ፤ በዐይናችሁ መልካምና ቅን የመሰለውን አድርጉብኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ እኔ ከሆነ ግን እነሆ፤ በእጃችሁ ነኝ፤ መልካምና ተገቢ መስሎ የሚታያችሁን ሁሉ አድርጉብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን፥ እነሆ፥ በእጃችሁ ነኝ፤ በዓይናችሁ መልካምና ቅን የመሰላችሁን አድርጉብኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ እኔ ጉዳይ እንደ ሆነ እነሆ በእናንተ እጅ ነኝ፤ ትክክልና ቀና መስሎ የታያችሁን ሁሉ አድርጉብኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን፥ እነሆ፥ በእጃችሁ ነኝ፥ በዓይናችሁ መልካምና ቅን የመሰለውን አድርጉብኝ። |
እንዲሁም ንጉሡ ኢዮአስ አባቱ ኢዮአዳ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፤ ልጁንም አዛርያስን አስገደለው፤ እርሱም ሲሞት፥ “እግዚአብሔር ይየው፤ ይፍረደውም” አለ።
ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነቱ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚች ከተማ፥ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በርግጥ ዕወቁ።”