ኤርምያስ 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ነቢዩና ካህኑም ረክሰዋልና፥ በቤቴም ውስጥ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነቢዩም፣ ካህኑም በጽድቅ መንገድ የማይሄዱ ናቸው፤ በቤተ መቅደሴ እንኳ ሳይቀር ክፋታቸውን አይቻለሁ።” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢዩና ካህኑም ረክሰዋልና፥ ሌላው ቀርቶ በቤቴ ውስጥ እንኳ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የነቢያቱና የካህናቱ መንፈሳዊ ሕይወት ተበላሽቶአል፤ ሌላው ቀርቶ በቤተ መቅደስ ውስጥ እንኳ ክፉ ነገርን ያደርጋሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢዩና ካህኑም ረክሰዋልና፥ በቤቴም ውስጥ ክፋታቸውን አግኝቻለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እግዚአብሔርም ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን፥ “በዚህ ቤትና ከእስራኤል ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለዓለም አኖራለሁ፤
የይሁዳም ታላላቅ ሰዎች ካህናቱና የሀገሩም ሕዝብ በአሕዛብ ርኵሰት ሁሉ መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ያለውን የእግዚአብሔርን ቤት አረከሱ።
ከካህናቱም ወገን ልጆች እንግዶቹን ሴቶች ያገቡ ሰዎች ተገኙ፤ ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ልጆችና ከወንድሞቹ ማዓሥያ፥ አልዓዛር፥ ኦሬም፥ ገዳልያ።
ወዳጄ በቤቴ ውስጥ ለምን ርኵሰትን አደረገች? ስእለት ወይም የተቀደሰ ሥጋ ክፋትሽን ከአንቺ ያስወግዳልን? ወይስ በእነዚህ ታመልጫለሽን?
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ከኢየሩሳሌም ነቢያት ዘንድ ርኵሰት በምድር ሁሉ ላይ ወጥቶአልና ሕማምን አበላቸዋለሁ፤ መራራ ውኃንም አጠጣቸዋለሁ።”
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
“ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፤ በተራሮችም ላይ የተቅበዘበዙ አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኮረብታ ዐለፉ፤ በረታቸውንም ረሱ።
ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ኀጢአትን አድርገዋልና፥ ከሐሳዊ ነቢይ ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ሐሰትን አደረጉ።
የይሁዳ ልጆች በፊቴ ክፉ ነገርን ሠርተዋል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ያረክሱትም ዘንድ ስሜ በተጠራበት ቤት ርኵሰታቸውን አኑረዋል።
ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ።
ሬስ። አቤቱ፥ እይ፤ ተመልከት ማንን እንዲህ ቃረምህ? በውኑ ሴቶች የማኅፀናቸውን ፍሬ፥ ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይበላሉን? በውኑ ካህኑና ነቢዩ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ይገደላሉን?
ልጆቻቸውንም ለጣዖቶቻቸው በሠዉ ጊዜ ፥ በዚያው ቀን ያረክሱት ዘንድ ወደ መቅደሴ ገቡ፤ እነሆም በቤቴ ውስጥ እንደዚህ አደረጉ።
ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስራኤልም በሳቱ ጊዜ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋውያን ሳይቀር ኀጢአታቸውን ይሸከማሉ።
የክብሩንም ጌጥ ወደ ትዕቢት ለወጡ፤ የርኵስነታቸውንም ምስሎች አደረጉባት፤ ስለዚህ እኔ በእነርሱ ዘንድ ርኩስ አድርጌአታለሁ።
በፊታቸውም ከእስራኤል ቤት ሽማግሌዎች ሰባ ሰዎችና የሳፋን ልጅ ያእዛንያ ቆመው ነበር፤ ሰውም ሁሉ እያንዳንዱ በእጁ ጥናውን ይዞ ነበር፥ የዕጣኑም ጢስ ሽታ ይወጣ ነበር።
ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ውስጠኛው አደባባይ አመጣኝ፤ እነሆም በእግዚአብሔር መቅደስ መግቢያ ፊት በወለሉና በመሠዊያው መካከል ሃያ አምስት የሚያህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀርባቸውም ወደ እግዚአብሔር መቅደስ፥ ፊታቸውም ወደ ምሥራቅ ነበረ፤ እነርሱም ወደ ምሥራቅ ለፀሐይ ይሰግዱ ነበር።