La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 22:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይህ​ንም ነገር ብታ​ደ​ርጉ፥ በዳ​ዊት ዙፋን የሚ​ቀ​መጡ ነገ​ሥ​ታት በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች ላይ ተቀ​ም​ጠው፥ በዚህ ቤት በሮች ይገ​ባሉ፤ እነ​ር​ሱም፥ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቻ​ቸ​ውም፥ ሕዝ​ቡም እን​ዲሁ ይገ​ባሉ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህን ትእዛዞች በሚገባ ብትጠብቁ፣ በዳዊት ዙፋን ላይ የሚቀመጡ ነገሥታት፣ ከመኳንንታቸውና ከሕዝባቸው ጋራ በሠረገሎችና በፈረሶች ተቀምጠው በዚህ ቤተ መንግሥት በሮች ይገባሉ፤ ይወጣሉም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህንንም ነገር በጥንቃቄ ብታደርጉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡ ነገሥታት፥ በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው፥ በዚህ ቤት በሮች ይገባሉ፤ እርሱም ባርያዎቹም ሕዝቡም እንዲሁ ይገባሉ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ልክ እኔ እንዳዘዝኳቸው ብታደርጉ፥ የዳዊት ዘሮች ከዙፋናቸው አይወርዱም፤ እንደ ወትሮው ሁሉ ከመኳንንቱና ከሕዝቡ ጋር በሠረገሎችና በፈረሶች ላይ በመቀመጥ በዚህ ቤተ መንግሥት የቅጽር በሮች መግባት ትችላላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይህንንም ነገር ብታደርጉ፥ በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡ ነገሥታት፥ በሰረገሎችና በፈረሶች ላይ ተቀምጠው፥ በዚህ ቤት በሮች ይገባሉ፥ እርሱም ባሪያዎቹም ሕዝቡም እንዲሁ ይገባሉ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 22:4
2 Referencias Cruzadas  

በዳ​ዊት ዙፋን ላይ የሚ​ቀ​መጡ ነገ​ሥ​ታ​ትና መሳ​ፍ​ንት በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች ላይ እየ​ተ​ቀ​መጡ በዚ​ህች ከተማ በሮች ይገ​ባሉ፤ እነ​ር​ሱና አለ​ቆ​ቻ​ቸው የይ​ሁ​ዳም ሰዎች፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የሚ​ቀ​መጡ ይገ​ባሉ፤ ይህ​ችም ከተማ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች።


በዳ​ዊት ዙፋን የም​ት​ቀ​መጥ የይ​ሁዳ ንጉሥ ሆይ! አን​ተና አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በእ​ነ​ዚ​ህም በሮች የሚ​ገባ ሕዝ​ብህ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።