ኤርምያስ 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስለዚህ እንደ ገና ከእናንተ ጋር እከራከራለሁ፤ ከልጆቻችሁም ልጆች ጋር እከራከራለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ እንደ ገና ከእናንተ ጋራ እፋረዳለሁ፤ ከልጅ ልጆቻችሁም ጋራ እከራከራለሁ።” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስለዚህ ከእናንተ ጋር ገና እከራከራለሁ፥ ይላል ጌታ፥ ከልጆቻችሁም ልጆች ጋር እከራከራለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር ገና እናንተን ሕዝቤን እወቅሳለሁ፤ በልጆቻችሁም ላይ ወቀሳ አቀርባለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ከእናንተ ጋር እከራከራለሁ፥ ከልጆቻችሁም ልጆች ጋር እከራከራለሁ። |
አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤
እግዚአብሔርም ደግሞ ከይሁዳ ጋር ይዋቀሳል፤ ያዕቆብንም እንደ መንገዱ ይበቀለዋል፤ እንደ ሥራውም ይከፍለዋል።
እናታችሁ ሚስቴ አይደለችምና፥ እኔም ባልዋ አይደለሁምና እናታችሁን ተዋቀሱአት። ዝሙቷን ከፊቷ፥ ምንዝርናዋንም ከጡቶችዋ መካከል አስወግዳለሁ።
እናንተ የእስራኤል ልጆች ሆይ! እውነትና ምሕረት፥ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድር ስለሌለ እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚኖሩትን ይወቅሳልና የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።
ተራሮች ሆይ፥ ጠንካሮች የምድር መሠረቶችም ሆይ፥ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፥ ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳልና የእግዚአብሔርን ክርክር ስሙ።