La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 15:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዳ​ር​ቻህ ሁሉ ስላለ ኀጢ​አ​ትህ ሁሉ ፋንታ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ህ​ንና መዝ​ገ​ብ​ህን ለመ​በ​ዝ​በዝ በከ​ንቱ እሰ​ጣ​ለሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በመላ አገርህ፣ ስላለው ኀጢአትህ ሁሉ፣ ሀብትና ንብረትህን፣ ያለ ዋጋ አሳልፌ ለምርኮ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“በመላ ግዛቶችህ ውስጥ ስላለ ኃጢአትህ ሁሉ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለብዝበዛ በከንቱ አሳልፌ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “በመላ ሀገሪቱ በፈጸማችሁት ኃጢአት ምክንያት ሀብታችሁንና ንብረታችሁን ያለ አንዳች ማካካሻ ለጠላት አሳልፌ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዳርቻህ ሁሉ ስላለ ኃጢአትህ ሁሉ ባለጠግነትህንና መዝገብህን ለመበዝበዝ በከንቱ እሰጣለሁ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 15:13
8 Referencias Cruzadas  

የጢ​ሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መን​ሻን ይዘው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። የም​ድር ባለ​ጠ​ጎች አሕ​ዛብ ሁሉ በፊ​ትሽ ይማ​ለ​ላሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በከ​ንቱ ተሸ​ጣ​ችሁ ነበር፤ ያለ ወር​ቅም እቤ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።”


ሕዝቤ በከ​ንቱ ተወ​ስ​ዶ​አ​ልና አሁን ከዚህ ምን አቆ​ማ​ችሁ?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ፤ ትጮ​ሃ​ላ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ስሜም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ሁል​ጊዜ ይሰ​ደ​ባል።


መበ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከባ​ሕር አሸዋ ይልቅ በዝ​ተ​ዋል፤ በብ​ላ​ቴ​ኖች እናት ላይ በቀ​ትር ጊዜ አጥ​ፊ​ውን አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ ጭን​ቀ​ት​ንና ድን​ጋ​ጤን በድ​ን​ገት አም​ጥ​ቼ​ባ​ታ​ለሁ።


በሜዳ ያለው ተራ​ራዬ ሆይ! ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ህ​ንና መዝ​ገ​ብ​ህን ሁሉ፥ የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገ​ጃ​ዎ​ች​ህ​ንም ስለ ኀጢ​አ​ትህ በድ​ን​በ​ሮ​ችህ ሁሉ ለመ​በ​ዝ​በዝ እሰ​ጣ​ለሁ።


የዚ​ች​ንም ከተማ ኀይል ሁሉ፥ ጥሪ​ቷ​ንም ሁሉ፥ ክብ​ር​ዋ​ንም ሁሉ፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ነገ​ሥ​ታት መዝ​ገብ ሁሉ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ እነ​ርሱ ይበ​ዘ​ብ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ ይዘ​ውም ወደ ባቢ​ሎን ያስ​ገ​ቡ​አ​ቸ​ዋል።


ሳባና ድዳን፥ የተ​ር​ሴ​ስም ነጋ​ዴ​ዎች፥ መን​ደ​ሮ​ች​ዋም ሁሉ፦ ምር​ኮን ትማ​ርክ ዘንድ መጥ​ተ​ሃ​ልን? ብዝ​በ​ዛ​ንስ ትበ​ዘ​ብዝ ዘንድ፥ ብር​ንና ወር​ቅ​ንስ ትወ​ስድ ዘንድ፥ ከብ​ት​ንና ዕቃ​ንስ ትወ​ስድ ዘንድ፥ እጅ​ግስ ብዙ ምርኮ ትማ​ርክ ዘንድ ወገ​ን​ህን ሰብ​ስ​በ​ሃ​ልን? ይሉ​ሃል።”


ብልጥግናቸውም ለምርኮ ይሆናል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፣ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይቀመጡባቸውም፣ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።