ኤርምያስ 13:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከብዙ ቀንም በኋላ እግዚአብሔር፥ “ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፥ በዚያም ትሸሽጋት ዘንድ ያዘዝሁህን መታጠቂያ ከዚያ ውስጥ ውሰድ” አለኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከብዙ ቀን በኋላም እግዚአብሔር፣ “ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፤ በዚያ እንድትሸሽገው የነገርሁህን መቀነት አምጣ” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከብዙ ቀንም በኋላ ጌታ፦ “ተነሣ፥ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፥ በዚያም እንድትሸሽገው ያዘዝሁህን መታጠቂያ ከዚያ ውስጥ ውሰድ” አለኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከብዙ ቀኖች በኋላም እግዚአብሔር፥ “ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተመልሰህ ሂድና መታጠቂያውን ውሰድ” አለኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከብዙ ቀንም በኋላ እግዚአብሔር፦ ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፥ በዚያም ትሸሽጋት ዘንድ ያዘዝሁህን መታጠቂያ ከዚያ ውስጥ ውሰድ አለኝ። |
እኔም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ሄድሁ፤ ቈፈርሁም፤ ከቀበርሁበትም ስፍራ መታጠቂያዪቱን ወሰድሁ። እነሆም መታጠቂያዪቱ ተበላሽታ ነበር፤ ለምንም አልረባችም።
የጨለማና የነፋስ ቀን፥ የደመናና የጉም ቀን ነው፤ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፤ ከዘለዓለምም ጀምሮ እንደ እርሱ ያለ አልነበረም፤ ከእርሱም በኋላ እስከ ልጅ ልጅ ድረስ እንደ እርሱ ያለ አይሆንም።
ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፤ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሓ አልገቡም።