ኤርምያስ 13:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ ሄድሁ፤ በኤፍራጥስም ወንዝ አጠገብ ሸሸግኋት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እግዚአብሔር በነገረኝ መሠረት ወደ ኤፍራጥስ ሄጄ ሸሸግሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም እንዳዘዘኝ ሄድሁ በኤፍራጥስም አጠገብ ሸሸግሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ እግዚአብሔር ባዘዘኝ መሠረት ሄጄ በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ መታጠቂያውን ደበቅሁት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም እንዳዘዘኝ ሄድሁ በኤፍራጥስም አጠገብ ሸሸግኋት። |
ከብዙ ቀንም በኋላ እግዚአብሔር፥ “ተነሥተህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፥ በዚያም ትሸሽጋት ዘንድ ያዘዝሁህን መታጠቂያ ከዚያ ውስጥ ውሰድ” አለኝ።
እንዳዘዘኝም ትንቢት ተናገርሁ፤ ስናገርም ድምፅ ሆነ፤ እነሆም መናወጥ ሆነ፤ አጥንቶችንም እየራሱ በሆነ በሰውነቱ ከአጥንቶች ጋር አንድ አደረጋቸው።
አብርሃም በተጠራ ጊዜ ርስት አድርጎ ይወርሰው ዘንድ ወዳለው ሀገር ለመሄድ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚደርስም ሳያውቅ ሄደ።