እግዚአብሔርም የከለዳውያንን አደጋ ጣዮች፥ የሶርያውያንንም አደጋ ጣዮች፥ የሞዓባውያንንም አደጋ ጣዮች፥ የአሞንንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደደበት፤ በባሪያዎቹ በነቢያት ቃል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያጠፉት ዘንድ በይሁዳ ላይ ሰደዳቸው።
ኤርምያስ 12:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርስቴ እንደ ጅብ ጕድጓድ ናትን? ወይስ በዙሪያዋ የሚከቡአት የሽፍቶች ዋሻ ናትን? የምድር አራዊት ሁሉ ይበሉአት ዘንድ ተሰብስበው ይመጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርስቴ ሌሎች አሞሮች ሊበሏት እንደ ከበቧት፣ እንደ ዝንጕርጕር አሞራ አልሆነችምን? ሂዱ፤ የዱር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፤ እንዲቀራመቷትም አምጧቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርስቴ እንደ ዝንጉርጉር አሞራ ሆነችብኝን? አሞሮችስ በዙሪያዋና በላይዋ ሆነዋልን? ሂዱ፥ የምድር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፥ እንዲበሉም አምጡአቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የመረጥኳቸው ሕዝቤ በሁሉ አቅጣጫ በጭልፊቶች እንደ ተከበበች ወፍ ሆነዋል፤ ስለዚህ ሌሎችም የዱር አራዊት መጥተው ሥጋቸውን በመብላት እንዲደሰቱ ጥሩአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርስቴ እንደ ዝንጕርጕር አሞራ ሆነችብኝን? አሞሮችስ በዙሪያዋና በላይዋ ሆነዋልን? ሂዱ፥ የምድር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፥ ይበሉም ዘንድ አምጡአቸው። |
እግዚአብሔርም የከለዳውያንን አደጋ ጣዮች፥ የሶርያውያንንም አደጋ ጣዮች፥ የሞዓባውያንንም አደጋ ጣዮች፥ የአሞንንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደደበት፤ በባሪያዎቹ በነቢያት ቃል እንደ ተናገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ያጠፉት ዘንድ በይሁዳ ላይ ሰደዳቸው።
የትዕቢተኞች ሰዎች ዐይኖች ይዋረዳሉ፤ የሰዎችም ኵራት ትወድቃለች፥ በዚያም ቀን እግዚአብሔር ብቻ ከፍ ከፍ ይላል።
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቀን በትዕቢተኛውና በኵራተኛው ሁሉ ላይ ከፍ ባለውም ላይ ይሆናል፤ እነርሱም ይዋረዳሉ፤
ሰይፍን ለመግደል፥ ውሾችንም ለመጐተት፥ የሰማያትንም ወፎች፥ የምድርንም አራዊት ለመብላትና ለማጥፋት፥ አራቱን ዓይነት ጥፋት አዝዝባቸዋለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።
የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፤ በእርሱም ላይ ደነፉ፤ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፤ ከተሞቹንም አፈረሱ፤ የሚቀመጥባቸውም የለም።
ለጠላቶቻቸው እጅ፥ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
ፌ። ጽዮን እጅዋን ዘረጋች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ እግዚአብሔር በያዕቆብ ዙሪያ ያሉትን እንዲያስጨንቁት አዘዘ፤ ኢየሩሳሌም በመካከላቸው እንደ ረከሰች ሆናለች።