ኤርምያስ 11:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም፥ “በእጃችን እንዳትሞት በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር” ብለው ነፍሴን ስለሚሹ ስለ አናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንግዲህ ሕይወትህን ለማጥፋት ለሚሹና፣ ‘በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር፤ አለዚያ በእጃችን ትሞታለህ’ ለሚሉህ ለዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም፦ “በእጃችን እንዳትሞት በጌታ ስም ትንቢት አትናገር” ብለው ነፍስህን ስለሚሹ ስለ ዓናቶት ሰዎች አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእግዚአብሔር ስም ትንቢት የተናገርክ እንደ ሆነ እንገድልሃለን” ብለው የኤርምያስን ሕይወት ለማጥፋት ስለሚፈልጉት ስለ አናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም፦ በእጃችን እንዳትሞት በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር ብለው ነፍስህን ስለሚሹ ስለ ዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ እቀጣቸዋለሁ፥ |
በብንያም ሀገር በዓናቶት ከነበሩ ካህናት ወገን ወደ ሆነ ወደ ኬልቅያስ ልጅ ወደ ኤርምያስ የመጣ የእግዚአብሔር ቃል።
በእኔ ላይ የተሰበሰቡና የከበቡኝን የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁ፤ መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፥ “ምናልባት ይታለል እንደ ሆነ፥ እናሸንፈውም እንደ ሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደ ሆነ፥ ተነሡ እኛም እንነሣለን” ይላሉ።
ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ይናገር ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘውን ነገር ሁሉ በፈጸመ ጊዜ ካህናትና ነቢያተ ሐሰት፥ ሕዝቡም ሁሉ፥ “ሞትን ትሞታለህ” ብለው ያዙት።
“እነሆ የአጎትህ የሰሎም ልጅ አናምኤል ወደ አንተ መጥቶ፦ ትገዛው ዘንድ የመቤዠቱ መብት የአንተ ነውና በዓናቶት ያለውን እርሻዬን ግዛ” ይልሃል።
ለጠላቶቻቸው እጅ፥ ነፍሳቸውንም ለሚሹአት እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ሬሳቸውም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት መብል ይሆናል።
“እናንተ ግን ለእኔ የተለዩትን የወይን ጠጅ አጠጣችኋቸው፤ ነቢያቱንም፥ “ትንቢትን አትናገሩ ብላችሁ ከለከላችኋቸው።