ያዕቆብም ልብን፥ ለውዝ፥ ኤርሞን ከሚባሉ ዕንጨቶች ርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው።
ኤርምያስ 1:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል፥ “ኤርምያስ ሆይ! ምን ታያለህ?” እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም፥ “የሎሚ በትር አያለሁ” አልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔር ቃል፣ “ኤርምያስ ሆይ፣ ምን ታያለህ?” ሲል ወደ እኔ መጣ። እኔም፣ “የአልሙን በትር አያለሁ” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞ የጌታ ቃል፦ “ኤርምያስ ሆይ! ምን ታያለህ?” እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም “የለውዝ በትር አያለሁ” አልኩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “ኤርምያስ ሆይ! የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “የለውዝ ቅርንጫፍ አያለሁ” አልኩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞ የእግዚአብሔር ቃል፦ ኤርምያስ ሆይ፥ ምን ታያለህ? እያለ ወደ እኔ መጣ። እኔም፦ የለውዝ በትር አያለሁ አልሁ። |
ያዕቆብም ልብን፥ ለውዝ፥ ኤርሞን ከሚባሉ ዕንጨቶች ርጥብ በትርን ወስዶ በበትሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እንዲታይ ነጭ ሽመልመሌ አድርጎ ላጣቸው።
ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ነው፤ የምሻውን እስኪያደርግ ድረስ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም፤ መንገዴንና ትእዛዜን አከናውናለሁ።
እግዚአብሔርም፥ “ኤርምያስ ሆይ! የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “በለስን አያለሁ፤ እጅግ መልካም የሆነ መልካም በለስ፥ ከክፋቱም የተነሣ ይበላ ዘንድ የማይቻል እጅግ ክፉ የሆነ ክፉ በለስ ነው” አልሁ።
እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ እናገራለሁ፤ የምናገረውም ቃል ይፈጸማል፤ ደግሞም አይዘገይም፤ እናንተ ዐመፀኛ ቤት ሆይ! በዘመናችሁ ቃሌን እናገራለሁ፤ እፈጽመውማለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ስለዚህ በላቸው፥ “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የምናገረው ቃል ይፈጸማል እንጂ ከቃሌ ሁሉ ደግሞ የሚዘገይ የለም፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
“እነሆ ቀኑ ደርሶአል፤ እነሆ! የእግዚአብሔር ቀን ወጥታለች፤ ስብራትህ ደርሶአል፤ ብትርም አብባለች፤ ስድብም በዝቶአል።
እግዚአብሔርም፥ “አሞጽ ሆይ! የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “ቱንቢ ነው” አልሁ። ጌታም፥ “እነሆ! በሕዝቤ በእስራኤል መካከል ቱንቢ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ደግሞ ይቅር አልላቸውም።
እርሱም፥ “አሞጽ ሆይ! የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ዕንቅብ ነው” አልሁት። እግዚአብሔርም አለኝ፥ “ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ ይቅር አልላቸውም።
እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፣ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፣ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው።
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴና አሮን ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገቡ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች የአሮን በትር አቈጠቈጠች፤ ለመለመችም፤ አበባም አወጣች፤ የበሰለ ለውዝም አፈራች።